አቶ ማሞ ይንበርበሩ (ማሞ ካቻ ) ማናቸው
አቶ ማሞ ይንበርብሩ (ማሞ ካቻ) አቶቢሲ ማሞ ካቻ፣ የት ትሄዳለህ? ገብረ ጉራቻ... ታዳጊው ማሞ ይንበርበሩ ገና በጨቅላ እድሜው አባቱ አቶ ይንበርበሩ በሥራ ምክ ንያት ወደ ኢሊባቦር ጎሬ ሲዛወሩ አብሮ ሄደ።
የአድዋ ጦርነት የትኛው ብሔር እነማንን አሰለፈ ?
ለመሆኑ የዓድዋ ጦርነት የጦር መሪዎች እነማን ነበሩ? ከየትኛው ነገድስ የተገኙ ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሩቅ ሳንሄድ የዘመቻው ጠቅላይ አዛዥና የጦሩ መሪ የሆኑት
የንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ ታሪከ ነገሥት የነበሩት ኦሮሞው ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊ ያዘጋጁትን የወቅቱን የንጉሡን ታሪከ ነገሥት ማንበቡ በቂ ነው። ከንጉሡ ታሪከ ነገሥት በላይ ስለ ዓድዋ ጦርነት መሪዎች ሊነግረን የሚችል ቀዳሚ ምንጭ ሊኖር አይችልም።
የዳግማዊ ምኒልክ ታሪከ ነገሥት የነበሩት ኦሮሞው ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊ ያዘጋጁትን ታሪከ ነገሥት ከምዕራፍ ፷ እስከ ፷፭ ስናነብ በዓድዋ ጦርነት ከተሰለፉት የጦር አበጋዞች ውስጥ በነገድ ኦሮሞ የሆነ የጦር መሪ የምናገኘው ሁለት ሰዎችን ብቻ ነው። እኒህ የጦር መሪዎችም እናቶቻቸው አማራ የኾኑት ሻቃ ኢብሳና አፈ ንጉሥ ነሲቡ መስቀሉ ናቸው። ከነዚህ ውጭ በታሪከ ነገሥቱ ወርድና ቁመት ስንወጣ ስንወርድ ብንውል ሌላ የኦሮሞ የጦር መሪ አናገኝም።
ኦነጋውያን የዓድዋ ጦርነት መሪዎቹ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው የሚል ተረት ከተስፋዬ ገብረአብ ተቀብለው መድገም የጀመሩት የጎጃሙን ንጉሥ፣ የወሎውን ንጉሥ፣ የመንዙን ተወላጅ፣ ወዘተ ሁሉ ዘሮቻቸው በሕይዎት እያሉ ታሪካቸውን በሞጋሳ ኦሮማይዝድ እያደረጉ ነው።
ከታች የታተመው ስዕላዊ መግለጫ የዐይን ምስክሩ ኦሮሞው ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊ ባዘጋጁት ታሪከ ነገሥት ውስጥ ከምዕራፍ ፷ እስከ ፷፭ ያለውን ታሪክ ጠቅልሎ የያዘና የዓድዋ አዝማቾች እነማን እንደነበሩ የሚያሳይ ቀዳሚ ምንጭ ነው።
ስዕላዊ መግለጫው ከመሀል አገር በዳግማዊ ምኒልክ መሪነት የዘመቱት የዓድዋ የጦር መሪዎችን ዝርዝር በሙሉ የያዘ ሲሆን እያንዳንዱ የጦር መሪ በየትኛው ግንባር እንደተሰለፈም ያሳያል።
እንደ ታሪኩ ሁሉ ይህ ስዕላዊ መግለጫም ተሚገኘው ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊ ባዘጋጁት የዳግማዊ ምኒልክ ታሪከ ነገሥት ውስጥ ምዕራፍ ፷ ከሚጀምርበት ገጽ በፊት ባለው የታሪከ ነገሥቱ ክፍል ነው።
በስዕላዊ መግለጫው ላይ የተዘረዘሩት የዓድዋ የጦር መሪዎች ስማቸው እንደሚከተለው ይቀርባል፤
1. ራስ መኮነን ወልደ ሚካዔል ወልደ መለኮት [አማራ]
2. ፊታውራሪ ገበዬሁ ክንዴ የግድም ወርቅ [አማራ]
3. ራስ ሚካኤል አሊ አመዴ [አማራ] (የራስ ሚካዔል [የኋላው ንጉሥ ሚካዔል] አባት ኢማም አሊ አመዴ የዐፄ ፋሲል የልጅ ልጅ ናቸው)
4. አፈ ንጉስ ነሱቡ መስቀሎ [ኦሮሞ]
5. ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ[ጉራጌ ]
6. ደጃዝማች ተሰማ ናደው [አማራ]
7. ባላምባራስ አጥናፌ ተክለ ዮሐንስ [አማራ]
8. ደጃዝማች በሻህ አቦዬ [አማራ]
9. ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት /አዳል ተሰማ ጎሹ ዘውዴ ስልጣን/ [አማራ]
10. ደጃዝማች ወልዴ አሻግሬ [አማራ]
11. ደጃዝማች ጫጫ አቦዬ [አማራ] (መንዜ ናቸው)
12. ደጃዝማች ውቤ አጥናፍ ሰገድ [አማራ]
13. ራስ ቢትወደድ መንገሻ [አማራ]
14. ራስ ወሌ ቡጡል ኃይለ ማርያም ገብሬ ተስፋ [አማራ]
15. ፊታውራሪ ተክሌ [አማራ]
16. ቱርክ ባሻ ታምሬ [አማራ]
17. አጋፋሪ ወልደ ገብርዔል በሻህ [አማራ]
18. ባሻ ገድሌ [አማራ]
19. ሊቀ መኳስ አድነው [አማራ]
20. ሊቀ መኳስ አባተ ቧያላው ንጉሡ [አማራ]
21. በጅሮንድ ባልቻ [ ጉራጌ]
22. ባላምባራስ ወሰኔ [አማራ]
23. ደጃዝማች ገሠሠ ወልደሐና [አማራ]
24. ባላምባራ አየለ [አማራ]
25. አዝማች ዛማኑኤል [አማራ]
26. በጅሮንድ ከተማ [አማራ]
27. ባላምባራስ ባንቴ [አማራ] (በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበሩት የፊታውራሪ ተሰማ ባንቴ አባት)
28. አዛዥ በዛብህ [አማራ]
29. ቀኛዝማች መኮነን [አማራ]
30. አሳላፊ ገበዬሁ [አማራ]
31. ልጅ ናደው [አማራ]
32. ሻቃ ኢብሳ [ኦሮሞ]
የኦነጋውያንን ተረት እየደገመ ከ፶ በመቶ በላይ የሚሆነው የዓድዋ ዘማችና የጦር መሪ ኦሮሞ እንደነበር ሊነግረን የሚቃጣው ዮናታን ተስፋዬ በታሪከ ነገሥቱ ውስጥ ያልተጠቀሰና እኛ የማናውቀው እሱ ግን የሚያውቃቸው የዓድዋ ጦር መሪዎች ካሉ ካልነገረ በስተቀር በንጉሠ ነገሥቱ ታሪከ ነገሥት የተመዘገበው ቀዳሚ የታሪክ ምንጭ የሚነግረን ታሪክ ቢኖር በዓድዋ ጦርነት መሪ ሆነው የዘመቱ የኦሮሞ ነገድ ተወላጆች ቁጥር ሁለት ብቻ ነው።
ከዚህ በስተቀር ዘሮቻቸው ጠፍተው ሳያልቁ የጎጃሙን ንጉሥ፣ የወሎውን ንጉሥ፣ የመንዙን ተወላጅ፣ የጉራጌውን አርበኛና የስሜኑን ባላባት እየቀሙ ኦሮሞ ለማድረግ መሞከር ለማሰብ ፍቃደኛ ያልሆነውን መንጋ ለማታለልና ለማሳሳት ካልጠቀመ በስተቀር የሚቀይረው የታሪክ እውነት አይኖርም።
ከላይ ከቀረበው የታሪከ ነገሥቱ ኦፊሻላዊ ቀዳሚ የታሪክ ምንጭ በተማሪ የዘመኑ የታሪክ ጸሐፊ ፕሮፈሰር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ "ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ" በሚል በ1901 ዓ.ም. በሮማ ባሳተሙ መጽሐፍ የዓድዋ ዘማቾች ከየትኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንደዘመቱ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፤
" የትግሬ ነፍጠኛ፣ የሸዋ ፈረሰኛ፣ የጎጃም እግረኛ፣ የቤተ አማራ ስልተኛ ከቦ ይቀላው፣ ያናፋው፣ ያንደገድገው ጀመር። ከእንዝርት የቀለለ የጁየ፣ ከነብር የፈጠነ ቤጌምድሬ፣ ከቋንጣ የደረቀ ትግሬ፣ ከአሞራ የረበበ ሽዌ፣ ከንብ የባሰ ጎጃሜ እያባረረ [ጥሊያንን] በየጎዳናው ዘለሰው። [ጥሊያኑም] አውሬ የነጨው ነጭ መንጋ እየመሰለ በየዱር ሆዱን ገልብጦ ወደቀና የአሞራ ቀለብ ሆነ። የመጣው መድፍ ሁሉ ከጥይቱ ከነመንኮራኩሩ በየመንገዱ እየወደቀ ተገኘ።...እንኳን በመከራ በደስታ ቢሆን ሁለት ለሊትና አንድ መአልት ከራብና ከጥም ጋራ አይቻልም።
የባራቲየሪን መሸሽና የጦሩን መመታት ባየ ጊዜ ያ ሁሉ ወደኋላ የነበረ የጣሊያን መድፈኛ መጫኛውን በጎራዴ እየቆረጠ መድፉን እየጣለ በመድፉ ስፍራ እሱ እየተተካ በአጋሰሱ እየጋለበ አስመራው ገባ። ካንድ ላይ ብቻ አስራ ስምንት መድፍ አንድ ጊዜ ሳይተኮስ እስከ ጥይቱ እስከ መንክራኩ ወድቆ ቀርቶ ተያዘ . . ."
ከዚህ የፕሮፌሰር አፈወርቅ የታሪክ መዝገብ፣ ቀዳሚ የታሪክ ምንጭና የዐይን ምስክርነት የዓድዋ ድል የተገኘው በተወርዋሪ የትግሬ ነፍጠኞች፣ ከአሞራ በፈጠኑ ሸዌዎች፣ ከንብ በባሱ ተናዳፊ ጎጃሜዎች፣ ከነብር በፈጠኑ ጎንደሬዎችና በስልት አዋቂ ቤተ አማሮች ተጋድሎ እንጂ በኦነጋውያን የፈጠራ ታሪክ እንዳልኾነ መገንዘብ ይቻላል ።
አቶ ማሞ ይንበርብሩ (ማሞ ካቻ) አቶቢሲ ማሞ ካቻ፣ የት ትሄዳለህ? ገብረ ጉራቻ... ታዳጊው ማሞ ይንበርበሩ ገና በጨቅላ እድሜው አባቱ አቶ ይንበርበሩ በሥራ ምክ ንያት ወደ ኢሊባቦር ጎሬ ሲዛወሩ አብሮ ሄደ።
ዘመናዊ ሸማቂዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? የደፈጣ (ሽምቅ) ውጊያ መሠረታዊ መርሆዎች የዘመናዊ ደፈጣ ግቦች ምንድናቸው በቂ ማብራሪያ ይዘን መጠናል መልካም ንባብ
የሸዋ ሉል መንግሥቱ የሸዋ ልዑል መንግሥቱ ጠለቅ ያለ የሥነ ጽሑፍ ዝንባሌ ያላት ከመሆኑም በላይ ለሙዚቃ ያላት አስተያየት ከፍተኛ በመሆኑ ዜማ ዎችንና ግጥሞችን ትደርሳለች፤ በዚህ ሞያ የምታገለግለው በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነትና ማስታወቂያ ክፍል የምሥራቅ በረኛ ፖሊስ መጽሔት ም/አዘጋጅነትና በሙዚቃው ክፍል ዜማና ግጥሞችን በመድረስ እንደዚሁም ልዩ ልዩ የአደባባይ ትር ኢቶችን በማዘጋጀት ነው፤ ይህም ሞያ ለሐገራችን ሴቶች እምብዛም የተለመደ አይደለም፥ የሸዋ ልዑል ግን «ልዩ ተሰጥኦዬ ነው» ነው ትላለች ፥ እስከዛሬ ድረስ ከደረሰቻቸው ግጥሞች ውስጥ በጣም የምትወደው (ያለም ባይተዋር ነኝ)