አቶ ማሞ ይንበርበሩ (ማሞ ካቻ ) ማናቸው
አቶ ማሞ ይንበርብሩ (ማሞ ካቻ) አቶቢሲ ማሞ ካቻ፣ የት ትሄዳለህ? ገብረ ጉራቻ... ታዳጊው ማሞ ይንበርበሩ ገና በጨቅላ እድሜው አባቱ አቶ ይንበርበሩ በሥራ ምክ ንያት ወደ ኢሊባቦር ጎሬ ሲዛወሩ አብሮ ሄደ።
#የጮቄ ስር ሙሽራዋ ደብረማርቆስ ከተማን በጨረፍታ ! ደብረ ማርቆስ ከተማ “ደብረ ማርቆስ" ከመባሏ በፊት ደጃዝማች ተድላ ጓሉ መንቆረር የሚለውን ስም እንደያዘች የመንግስታቸው መቀመጫ ትሆን ዘንድ መረጧት ። ደጃዝማች ተድላ ጓሉም ህይወታቸው እስከ አለፈበት ህዳር 6 ቀን 1860 ዓ/ም ድረስ መቀመጫቸውን መንቆረር አድርገው ገዙ። መንቆረር የሰው ስም መጠሪያ ነበር፡፡
#የጮቄ ስር ሙሽራዋ ደብረማርቆስ ከተማን በጨረፍታ !
ከ1872 ዓ.ም የመርቆሪዮስ ቤተ ክርስቲያን በመብረቅ ይቃጠላል፡፡ ይህን ተከትሎም ንጉስ ተክለ ሃይማኖት ጥር ወር 1872 ዓ.ም ከነገሡ በኋላ መልዕለተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሰረት አድርገዋል፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተ በኋላ በ1874 ዓ.ም የከተማዋ ስያሜ “መንቆረር” የሚለው ቀርቶ ደበረ ማርቆስ እንዲባል ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡ በውሳኔ ብቻ አልቀረም በመላ ከተማዋ ከዚህ በኋላ የከተማዋ ስም ደብረ ማርቆስ ተብሎ አንዲጠራ አዋጅ አሳውጀዋል፡፡
በንጉሱ ዘመን ደብረ ማርቆስ ከተማ የጎጃም ጠቅላይ ግዛት መናገሻ በመሆን አገልግላለች፡፡ ያኔ ቀበሌ የሚባል አልነበረምና በወቅቱም የነበረው የከተማዋ ስሪት (አስተዳድር) የዘውዳዊ ሥርዓት የተከተለ በመሆኑ የሰፈር ስያሜዎችም ይህንን የተከተሉ ነበር፡፡
ለደጅአዝማች፣ ለፊታውራሪና ለሌሎችም ሹማምንቶች እና መኳንንቶች ማህበራዊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሰዎች በከተማው ውስጥ የራሳቸው መንደርና ሰፈር ተስጥቷቸው ነበር፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-1ኛ. ካህን ሠፈር
ካህን ሰፈር እየተባለ ይጠራ የነበረው የከተማው ክፍል ከደብረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ደቡባዊ አቅጣጫ እስከ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል አካባቢ ያለው ነበር፡፡ ካህን ሰፈር ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ምርጥ ምርጥ ሀብታም ካህናት እንዲኖሩበት የተሰጠ በረከት ነው፡፡
ካህናቱ በከተማው ውስጥ የተለየ ቦታና ይዞታ እንዲሰጣቸው የተደረገበት ምክንያት የንጉሡ ሥርዓት ቤተ ክርስቲያን ሲሶ መንግሥት አላት የሚል አቋም ስላላቸውና ሃይማኖታዊ የመንግሥት ሥርዓት ስለሚያራምዱ ነበር፡፡
2ኛ. ፈረስ ቤት
ከቀድሞው ደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት እስከ ንጉሥ ተክለሃይማኖት ት/ቤት ያለውን አካባቢ ያጠቃልላል፡፡ በወቅቱ ሰው ያልሰፈረበትና እስከ ውትርን ወንዝ ድረስ ሜዳ ስለነበር ለሴራራ ነጋዴዎች ማረፊያ የተሰጠ ነበር፡፡ ሴራራ ነጋዴዎች በአህያ፣ በበቅሎና በድንጉላ ፈረሶች የሚነግዱ ሲሆን የንግድ መስመሩም አስከ ሱዳን ድረስ የዘለቀ ነበር፡፡ በተጨማሪም የደጃዝማች፣ የፊታውራሪ እና የሌሎች ሹማምንቶች የጭን በቅሎና ፈረሶች ማረፊያና መሰማሪያ ነበር፡፡
3ኛ. ቅሬ ሠፈር
የአሁኑን ቀበሌ 2 እስከ 6 ያለውን አካባቢ የሚያዋስን ሲሆን የከተማዋ የንግድ ማዕከል ነበር፡፡ በተለይ ጠላ፣ ጠጅና የሐበሻ አረቄ በሽያጭ የሚገኝበት ቅሬ ሰፈር ነበር፡፡ በወቅቱ የንግዱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ገበያ ለመሳብ ኮማሪዎች ወይም መጠጥ ለመሸጥ የተሰማሩ የአካባቢው ሴቶች ልባዊ ሳይሆን አፋዊ ጨዋታና ቀረቤታ ያሳዩ ስለነበር ነዋሪዎች ቅሬዎች ናቸው በማለት ሰየሟቸው፡፡ ስለሆነም ቅሬ ሠፈር ተብሎ ለረጅም ጊዜ ቆይቷል ።
4ኛ. ነጋሪት መቺ ሠፈር
ከቅዳምን (ዋናው የገበያ ማእከል) እስከ አብማ ሙሉ ሳይክል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ ቤት አካባቢ ያለው ነው፡፡ የንጉሡ ነጋሪት መችዎች ወይም ጎሳሚዎች ለመኖሪያነት በርስት የተሰጣቸው አካባቢ ነው፡፡ የቦታው ስያሜ የሰዎችን የስራ ተግባር በመውሰድ ጥቅም ላይ እንደዋለ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
5ኛ. ሰፊ መንደር
በንጉሡ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ለመኖሪያነት የተሰጠ አካባቢ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ሚኖሩ ሰዎች ለቤተ መንግሥት ባለሟሎችና ለከተማዋ ነዋሪዎች የፈረስና የበቅሎ ኮርቻዎችን፣ ዝናርና ሌሎች አልባሳትን የሚሰፉ ባለሙያዎች እንዲኖሩበት የተፈቀደ ቦታ ነው፡፡ ሰፊ መንደር በአሁኑ ቀበሌ 04 አስተዳድር ስር ተጠቃሎ ይገኛል ።
6ኛ. ተልባ ሠፈር
ከደበረ ማርቆስ ቤተክርስቲያን ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ያለው አካባቢ ነው፡፡ በእርሻ የተሰማሩ ሰዎች የሰፈሩበት አካባቢ ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ ለተልባ ምርት ከሁሉም በተሸለ ደረጃ ምቹ ስለነበር ለአካባቢው መጠሪያ እንደሆነ ይነገራል፡፡
7ኛ. ደመራ ሰፈር
ከአብማ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ የነበረ የሰፈር ስያሜ ነው፡፡ ከንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ ጀምሮ አመታዊው መስቀል ደመራ ይደመርበታል፡፡ ሰልፍም የሚካሄደው ደመራ ሰፈር አካባቢ እንደነበር ይነገራል፡፡
8ኛ. ኃይሉ ገበያ( ማክሰኝት) ሠፈር
ከእንድማጣ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን እስከ አውሮፕላን ማረፊያ ያለውን አካባቢ ያጠቃልላል፡፡ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት የነጋዴዎች መገናኛና የገበያ ቦታ እንዲሆን አድርገውት ነበር፡፡ ይሁን እንጅ በንግድ መነሀሪያነቱ ብዙም አልገፋም ነበር፡፡ ምክንያቱም አሁን 01 ቀበሌ ያለው ቅዳምን ገበያ ስለተረከበው ነበር፡፡
9ኛ. ግምጃ ቤት
ከደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል እስከ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ያለው አካባቢ የሚጠራበት ስያሜ ነው፡፡ ይህ ስያሜ አሁን ድረስ በአገልግሎት ላይ ይገኛል፡፡ ግምጃ ቤት ሠፈር በቀድሞው ጊዜ የሐሙስ ገበያ መቋሚያ በመሆን ያገለግል ነበር፡፡ በአጠቃላይ ደብረ ማርቆስ ከተማ ባሶ በርን ጨምሮ ከ14 ያላነሱ ሰፈሮች ነበሯት፡፡
የጎጃም ጠቅላይ ግዛት ማዕከል የሆነችውን ደብረ ማርቆስ ብለው የሰየሙትና ጎጃምንና ከፋን ያስተዳድሩ የነበሩት ንጉስ ተክለ ሃይማኖት የልጅነት ስማቸው አዳል ተሰማ ነበር። አዳል ተሰማ እናቱ ወይዘሮ ምዕላድ ስትባል የአፄ እስክንድር ዘር ናት። አዳል የአባቱ የዘር ሃረጉ የሚመዘዘው ከጎጃሙ ልዑል ዮሴደቅ ወልደ አቢብ እና ከጎንደሯ ንግስት ዳግማዊት ወለተ እስራኤል ነው። ታላቁ ዮሴዴቅ በአንድ ወቅት ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረ ሆነ። ያኔ ጎንደሮች "ይኼንን ጉልበተኛ በጋብቻ ጉልበቱን እናብርደው" ብለው በማሰብ ዳግማዊት ወለተ እስራኤል የተባለች ቆንጆ ዳሩለት። እንደታሰበውን ዮሴዴቅ ጊዜውንም ጉልበቱን ዳግማዊት ወለተ እስራኤል ላይ አደረገ። ሙሽሮች ትዳራቸው ሰምሮ ታላቁ ራስ ኃይሉ ዮሴዴቅን ወለዱ። ታላቁ ራስ ኃይሉ ወይዘሮ ድንቅነሽ እና ደጃዝማች መርዕድን ወለዱ። መርዕድ ከፊሉን ጎጃም ሲያስተዳድር ወይዘሮ ድንቅነሽ ለዳሞቱ ባላባት እና አስተዳዳሪ ደጃዝማች ዘውዴ ተዳረች።
የወይዘሮ ድንቅነሽ ባል ደጃዝማች ዘውዴ የመርዕድን ግዛት በኃይል ነጥቆ የማስተዳደር ሃሳብ መጣለት። ደጃዝማች መርዕድ ግን የዋዛ አይደለም፥ ነገሩን ቀድሞ ሰምቷል። ደጃዝማች መርዕድ ታዲያ አምቻውን( የእህቱን ባል) ማሰር ፈለገና "እህቴን ድንቅነሽን ይዘሃት ናና ልያት" ሲል ላከበት። ዘውዴ ሚስቱን ከኋላው አስከትሎ "ከተፍ" አለ። መርዕድ ዘውዴን ቀራኒዮ አካባቢ አንድ ዋሻ ውስጥ ወስዶ በግዞት አስቀመጠው። ደጃዝማች ዘውዴ ሥልን ተቀምጦም ተኝቶም ድንቅነሽ ብቻ ማሰብ ሆነ ስራው። ፍቅሩ ሲጠናበት "ኮሶ ታምሜያለሁና ሚስቴ መጥታ መድሃኒቱን ትጋተኝ" ሲል ደጃዝማች መርዕድን ተማፀነ። ደጃዝማች መርዕድ ድንቅነሽን ላከለት። ወይዘሮ ድንቅነሽ በልቧ ትዝታዋን በማኃፀኗ ጎሹን ይዛ ወደ ደብረ ማርቆስ ተመለሰች። ወይዘሮ ድንቅነሽ ከዘጠኝ ወራት በኋላ ጎሹን ወደ ምድር አመጣችው፤ አደገ፤ አገባና ተሰማን ወለደ። ተሰማ ወይዘሮ ምዕላድን አግብቶ አዳል ተሰማን በ1839 ዓም ወለደ። አዳል ተሰማ ጎርምሶ ከቤት እስከሚወጣ ድረስ ያደገ ከቀድሞው የጎጃም ገዥ እና የደብረ ማርቆስ ከተማ መስራች ደጃዝማች ተድላ ቤት ነው።
ደጃዝማች ተድላ ጓሉ ጠንቃቃ ቤተክርስቲያን ሳሚ እና ሩህሩህ ነበሩ። ቤተክርስቲያን በማሰራት የታወቁ ናቸው። እሁድ ከቤተክርስቲያን አይቀሩም። የሞቱ ጊዜ ሞታቸው ለሰፊው ህዝብ ተደብቆ በድብቅ ነበር የውሽ ሚካኤል የተቀበሩት። ህዝቡ ግን ጭምጭምታ ሰምቶ ስለነበረ እንደዚህ አለ።
አልሞተም ይሉናል ደጃዝማች ተድላን
አሁን እሑድ ሲቀር የምናዬውን።
የደጃዝማችን ሞትን ተከትሎ ስልጣን የያዘው ልጅ ደስታ ተድላ በወቅቱ ከነበረው የኢትዮጵያ መሪ አፄ ተክለጊዮርጉስ ሊስማማ አልቻለም። አፄ ተክለጊዮርጊስ ነገሩን በጋብቻ ማብረድ ፈልገው ልጃቸውን እንዲያገባ ቢለምኑትም አሻፈረኝ አለ። በዚህ ጊዜ ብልሁ አዳል ተሰማ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ከአፄ ተክለጊዮርጊስ ጋር ተወዳጀ። የአፄ ተክለ ጊዮርጊስ እህት የሆነችውን ወይዘሮ ላቀች ገብረ መድኃንን ሚስት አደረገ። ወዲያውኑ አዳል የሚለው ስም ተቀይሮ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተባለ።
በ1839 ዓ.ም የተወለዱት ንጉስ ተክለሃይማኖት በ1872 ዓም የጎጃም እና የከፋ ገዥ ተብለው ነገሱ። ይሄኔ ነው እንግዲህ ንጉሥ ተክለሃማኖት በንግስናቸው ወቅት ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በከተማው መሰራቱን ተከትሎ የከተማይቱ ስም መንቆረር መባሉ ቀርቶ ደብረ ማርቆስ እንዲባል የአስደረጉት።
መሞት ከአዳም የወረስነው ነውና ንጉስ ተክለኃይማኖት ታመው ጥር ሦስት ቀን 1893 ዓ/ም ደብረ ወርቅ ማርያም ሞቱ። አስክሬናቸው ወደ ደብረ ማርቆስ መጥቶ ራሳቸቸ ባሰሩት የቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን አረፈ።
ደብረ ማርቆስ ብዙ ከተሞች መኪና የሚባል ነገር ሳያውቁ አውሮፕላን ማረፊያ ነበራት። ከ1937 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 1987 ዓም ድረስ መደበኛ በረራ አልተቋረጠም ነበር። ከ1988 እስከ 1995 ዓ/ም ድረስ ወጣ ገባ እያለ ቢቆይም ከ1996 ዓ.ም እሰከ 2014 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ከቆየ በኋላ ዘመኑን በዋጁ ልጆቿ አማካኝነት አሁን ላይ የአውሮፕላን ማረፊያ እየተገነባ ይገኛል፡፡
ደብረ ማርቆስ የጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዋና መዲና በመሆን ለብዙ ዘመን አገልግላለች። አሁን የከተማይቱ ድምቀት የሆነው የንጉስ ተክለሃይማኖትን አደባባይ ያሰሩት በኃይለ ስላሴ ዘመን ጎጃንም እንዲያስተዳድሩ በተሾሙት እና "አማራ አንገቱ አንድ ነው" በማለት የሚታወቁት የሸዋው አርበኛ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ ነው። ዐብዬ ብርሌ የተባለ የግሽ ዓባይ ተወላጅ በ1957 ዓም በደብረ ማርቆስ ከተማ የንጉስ ተክለሃይማኖት ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረበት ወቅት ፀሐዩ እንቁስላሴ የንጉስ ተክለሃይማኖት አደባባይን ሲያሰሩ በግል ጉዳይ የሚመጣውን ባላገር ሁሉ ድንጋይ እና አፈር ያሸክሙ እንደነበረ እና እራሳቸውም እየተዘዋወሩ ያስተባብሩ እንደነበረ ያዬውን "በሀገር ፍቅር ጉዞ" በተሰኘው መፅሐፉ አስፍሯል።
ደብረ ማርቆስ ከዓመት እስከ ዓመት ያለምንም ስራ ሲገማሸር የሚኖረውን የጨሞጋን ወንዝ ተጠቅማ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንድትችል በ2002 ዓ/ም ከቻይና መንግስት በተገኘ ብድር የጨሞጋ ሐይል ማመንጫ ሊገነባ ከስምምነት ላይ ተደርሶ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ በነበረው የወያኔ የረቀቀ ሴራ አማካኝነት ዕውን መሆን ባለመቻሉ የህዝብ ጥያቄ እንደሆነ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል ። ደብረ ማርቆስ በውስጧ ሰንተራ፣ እነራታ፣ ወንቃ፣ አባ አስራት ገዳም ፣ እንግጫ እና የመሳሰሉ ስመ ጥርና ታሪካዊ ሰፈሮች አሉ። ሰንተራ ድሮ እነ ተድላ ጓሉ ፈረስ ጉግስ የሚጫወቱበት ለጥ ያለ መስክ ሲሆን አሁን ላይ ከተማዋ የውሃ ምንጭ ነው። መስኩ አሁንም ከነ ግርማ ሞገሱ አለ። አባ አስራት ገዳም በ1816 ዓ/ም አካባቢ አባ አስራት በተባሉ አባት የተመሰረተ ገዳም ነው።
ፀሐዩ እንቁስላሴ ምንም እንኳ መሰረተ ልማት በመገንባት ጎበዝ ቢሆኑም ኃይለ ስላሴ በጣሉት የመሬት ግብር ብዙ አቤቱታ ይቀርብባቸዋል። አንድ ቀን ሰውነቴ የሚባል ግለሰብ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ ላይ አቤቱታ ይዞ ይቀርባል። በወቅቱ ኃይለኛ ዝናብ እየዘነበ ስለነበረ ደጃዝማች ፀሐዩ "አያ ሰውነቴ! ዝናቡ እንዳይመታህ ወደ ውስጥ ዝለቅ( ግባ)" ሲሉት አያ ሰውነቴ "ጌታዬ! እኔን የመታኝ ዝናቡ ሳይሆን ፀሐዩ ነው" ሲል በቅኔ የደጃዝማች ፀሐዩን በደለኛነት ተናገረ ይባላል። ቅሬታው ሲበረታ ጃንሆይ ኃይለስላሴ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴን አንስተውም ወደ ከፋ ወስደው በእሳቸው ፈንታ መጀመሪያ ደጃዝማች ደረጀ መኮነንን ቀጥሎም ልጅ የኃይለማርያም ከበደን ወደ ደብረ ማርቆስ ላኩ። ወዲያው ደርግ ገባ። ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁ ስላሴም ደርግ ጋር ገጥመው ህይወታቸው አለፈ።
ከ1943 ዓ.ም ጀምሮ (ከ1943-1949 ዓ.ም) በከንቲባ ፊታውራሪ ጊላ ጊዮርጊስ እቁቢት መመራት የጀመረቸው ደብረ ማርቆስ ከተማ እስካሁን በታሪኳ 23 ከንቲባዎችን አስተናግዳ አሁን ላይ በ24ኛው ከንቲባ እየተመራች ትገኛለች፡፡
በእድገት ማማ ላይ የምትጓዘው ደብረ ማርቆስ ከተማ የ"ሪጅኦፖሊታን" የከተማ የዕድገት ደረጃ ላይ ደርሳ በአራት ክፍለ ከተማዎችና በ20 ቀበሌዎች ተዋቅራ ትገኛለች። በአብማ ክፍለ ከተማ፣ በመንቆረር ክፍለ ከተማ፣ በደጃዝማች ተድላ ጓሉ ክፍለ ከተማ እና በንጉስ ተክለሃይማኖት ክፍለ ከተማ ስም ተሰይማ ትገኛለች ።
ከተማዋ ስትመሰረት የነበራት ስፋት 272 ሄክታር እየጨመረ ሂዶ እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ 6460 ሄክታር ደርሶ ነበር፡፡ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ግን ከተማዋ ርጅኦፖሊታን መሆኗን ተከትሎ የከተማዋ ስፋት ከ17 ሽህ ሄክታር በላይ ደርሷል፡፡ የህዝቧ ቁጥርም በፕላን ኮሚሽን ግመታዊ (Projection) ቆጠራ መሠረት ከ2 መቶ 85 ሽህ በላይ ደርሷል፡፡ አሁን ላይ ከተማዋ የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ አለኝታ የሆኑ ልዩ ኃይሎችና ፖሊሶች ማሰልጠኛ ማእከል የሆነ አንድ አማራ ፖሊስ ኮሌጅ፣ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል፣ የአንጋፋው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ በ1995 ለተመሰረተው የአንጋፋው መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እና የአንድ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ባለቤት ናት ። ደረጃውን የጠበቀ የጎጃም ባህል ግንባታም በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ወደር የሌለው ግዙፍ የዘይት ፋቭሪካም ተገንብቶ ይገኛል፡፡ 3 የዱቄት ፋቭሪካ፣ አንድ የብስኩት ፋቭሪካ፣ አንድ ግራናይት ፋቭሪካ እና ሌሎችም ፋቭሪካዎች ተጠናቀው በስራ ላይ ናቸው፡፡
በከተማው ወደ ዩኒቨርሲቲው መሄጃ መስመር የስነ ፅሑፍ አድባር የሆኑት የሃዲስ አለማየሁ የክብር ሃውልት ሌላው የከተማይቱ ድምቀት ሆኗል።
ደብረ ማርቆስ ከባህሏ ጋር የታረቀች፣ ወግና ልማዷን ጠብቃ የያዘች ከተማ ነች። የጎጃም የባህል ልብስ በያይነቱ ተለብሶ ይገኛል። ከተማዋ በፍቅር፣ በመቻቻል፣ በመተሳሰብና በአብሮነት ሁሉንም አቅፋ የያዘች ከተማ ናት፡፡ በውስጧ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የፕሮቴስታንት፣ የጅሆባ፣ የአድቬንቲስት እና የተሀድሶ ሃይማኖት ተከታዮች በፍቅር፣ በሰላምና በመተሳሰብ በአነድነት ይኖሩባታል፡፡
ከተማዋ ለኢንቨስትመንት ምቹ፣ አይሯ ተስማሚ፣ ነዋሪዎች ሰው አክባሪ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ መሬቱ ነጭ አብቃይ፣ ነግደው ሚያተርፉባት፣ ፋቭሪካ ገንብተው የሚበለጽጉባት ከተማ ናት፡፡
ለባለ ሀብቶች 353 ሄክታር ተለይቶ በ159.7 ሄክታር ብቻ ላይ የተገነባ ሲሆኑ 193.3 ሄክታር ባለሃብቶችን ይጠብቃል፡፡ እርስዎም በዚህች ታሪካዊና ውብ ከተማ መጥተው መዋዕለ ነዋየዎትን ቢያስቀምጡ (ቢያፈሱ) ከምንልዎት በላይ አትራፊና ባዕለ ጸጋ ይሆናሉ፡፡
አቶ ማሞ ይንበርብሩ (ማሞ ካቻ) አቶቢሲ ማሞ ካቻ፣ የት ትሄዳለህ? ገብረ ጉራቻ... ታዳጊው ማሞ ይንበርበሩ ገና በጨቅላ እድሜው አባቱ አቶ ይንበርበሩ በሥራ ምክ ንያት ወደ ኢሊባቦር ጎሬ ሲዛወሩ አብሮ ሄደ።
የሸዋ ሉል መንግሥቱ የሸዋ ልዑል መንግሥቱ ጠለቅ ያለ የሥነ ጽሑፍ ዝንባሌ ያላት ከመሆኑም በላይ ለሙዚቃ ያላት አስተያየት ከፍተኛ በመሆኑ ዜማ ዎችንና ግጥሞችን ትደርሳለች፤ በዚህ ሞያ የምታገለግለው በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነትና ማስታወቂያ ክፍል የምሥራቅ በረኛ ፖሊስ መጽሔት ም/አዘጋጅነትና በሙዚቃው ክፍል ዜማና ግጥሞችን በመድረስ እንደዚሁም ልዩ ልዩ የአደባባይ ትር ኢቶችን በማዘጋጀት ነው፤ ይህም ሞያ ለሐገራችን ሴቶች እምብዛም የተለመደ አይደለም፥ የሸዋ ልዑል ግን «ልዩ ተሰጥኦዬ ነው» ነው ትላለች ፥ እስከዛሬ ድረስ ከደረሰቻቸው ግጥሞች ውስጥ በጣም የምትወደው (ያለም ባይተዋር ነኝ)
የደብረ ሊባኖስ የመጀመሪያው ቤተከርስቲያን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በ1362 ዓ.ም.ተሰራ።