• 10 Oct, 2024

የሸዋ ልዑል መንግሥቱ

የሸዋ ልዑል መንግሥቱ

የሸዋ ሉል መንግሥቱ የሸዋ ልዑል መንግሥቱ ጠለቅ ያለ የሥነ ጽሑፍ ዝንባሌ ያላት ከመሆኑም በላይ ለሙዚቃ ያላት አስተያየት ከፍተኛ በመሆኑ ዜማ ዎችንና ግጥሞችን ትደርሳለች፤ በዚህ ሞያ የምታገለግለው በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነትና ማስታወቂያ ክፍል የምሥራቅ በረኛ ፖሊስ መጽሔት ም/አዘጋጅነትና በሙዚቃው ክፍል ዜማና ግጥሞችን በመድረስ እንደዚሁም ልዩ ልዩ የአደባባይ ትር ኢቶችን በማዘጋጀት ነው፤ ይህም ሞያ ለሐገራችን ሴቶች እምብዛም የተለመደ አይደለም፥ የሸዋ ልዑል ግን «ልዩ ተሰጥኦዬ ነው» ነው ትላለች ፥ እስከዛሬ ድረስ ከደረሰቻቸው ግጥሞች ውስጥ በጣም የምትወደው (ያለም ባይተዋር ነኝ)

inbound439845265328110297
የሸዋ ሉል መንግሥቱ

የሸዋ ልዑል መንግሥቱ ጠለቅ ያለ የሥነ ጽሑፍ ዝንባሌ ያላት ከመሆኑም በላይ ለሙዚቃ ያላት አስተያየት ከፍተኛ በመሆኑ ዜማ ዎችንና ግጥሞችን ትደርሳለች፤ በዚህ ሞያ የምታገለግለው በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነትና ማስታወቂያ ክፍል የምሥራቅ በረኛ ፖሊስ መጽሔት ም/አዘጋጅነትና በሙዚቃው ክፍል ዜማና ግጥሞችን በመድረስ እንደዚሁም ልዩ ልዩ የአደባባይ ትር ኢቶችን በማዘጋጀት ነው፤ ይህም ሞያ ለሐገራችን ሴቶች እምብዛም የተለመደ አይደለም፥ የሸዋ ልዑል ግን «ልዩ ተሰጥኦዬ ነው» ነው ትላለች ፥ እስከዛሬ ድረስ ከደረሰቻቸው ግጥሞች ውስጥ በጣም የምትወደው (ያለም ባይተዋር ነኝ) የተባለውን መሆኑን ገልጻልናለች ፡ በግጥሙ ውስጥ ፤

የምንከባከበው የውሸት ውበቴ
አይደለም ማስረጃ ለነዋሪነቴ
ድንገት ይሸሸኛል ለመሆን አፈር
ያልነበርኩ የማልኖር ያለም ባይተዋር ። የሚል ይገኝበታል ።

በዚህ ዓመት በግጥሞቼ በኩል አድናቆትን ያተርፋል ብዬ ተስፋ የማደርገው ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ርዕስ ተደርሶ መርዓዊ ዮሐንስ የሚያዜመው ነው ስትል አውግታናለች ።

በዚህ ሥራ የቆየቺው ሦስት ዓመት ሲሆን ፶፬ የዘፈን ግጥሞ ችና ፲፮ ዜማዎች አሏት ። ዘንድሮ ካዘጋጀቺው ዜማ አታውሩልን ሌላ የተሰኘቺው የባሕል ሙዚቃ ድንቅ ሳትሆን አትቀርም ብላናለች::

ስለ ሐገራችን ሙዚቀኞች ያላትን አስተያየት ተጠይቃ « የግጥሞች አንካሳነት የማይጠገን ስብራት ሆኖ ይሰማኛል ጥሩ ግጥም የሚመርጥ ድርጅት ቢቋቋም መልካም ነበር በሌላው በኩል ከተመ ለከትነው ሙዚቃችን ተሻሽሏል፡ነገር ግን ቃል ሙዚቃ ነው ሙዚቃም ቃል ነው ፡ የሚለው ባሁኑ ጊዜ ሥፍራ አላገኘም አዝማሪዎች መልእክት የለሽ ጩኸት ሲያሰሙ እበሽቃለሁ» ብላለች ። የሸዋ ልዑል እኔና ግጥሞቼ የሚለውን መጽሐፏን ለማሳተም በመዘጋጀት ላይ መሆኗን ገልጻለች ።

ባሁኑ ጊዜ በትርፍ ሰዓቷ ሐረር በሚገኘው የኢት/ ሬዲዮ የኦሮምኛ ቋንቋ ፕሮግራም የወይዛዝርትን ክፍለ ጊዜ በማዘጋጀት ትሠራለች በዚህም ከአድማጮች ያላት አስተያየት ከፍተኛ መሆኑ ታው ቋል ፥ እንደዚሁም ሐረር ለተቋቋመው የወጣቶች አገልግሎት ድርጅት በዚህ ዓመት ለኰሚቴ አባልነት ተመርጣለች ።

አጉል ፍርሃትና መቅለስለስ ፥ አሽሙጥና ፡ ጉራ ሴቶችን ወደ ኋላ የሚስቡ ልጓሞች ስለሆኑ በኔ ዘንድ ሥፍራ የላቸውም ትላለች የምትጠላው ነገር ኩራትና ነገ አደርገዋለሁ ማለት መሆኑን ትናገ ራለች።የሸዋሉል በኢትዮጵያ ራድዮና ቴሌቭዢን እንዲሁም በጋዜ ጦች የምትሰጠውና የሰጠችው ትችት በይበልጥ የሴት ጋዜጠኛነቷን ሊያረጋ ግጥላት ችሏል ።

የምትወደው ደግሞ በማናቸውም ጊዜ የትኛውም ሥፍራ ሕዝባዊ አገልግሎት ላይ መዋልን ነው ።