• 10 Oct, 2024

የደፈጣ (ሽምቅ) ውጊያ !

ዘመናዊ ሸማቂዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? የደፈጣ (ሽምቅ) ውጊያ መሠረታዊ መርሆዎች የዘመናዊ ደፈጣ ግቦች ምንድናቸው በቂ ማብራሪያ ይዘን መጠናል መልካም ንባብ

የደፈጣ (ሽምቅ) ውጊያ !

የደፈጣ (ሽምቅ) ውጊያ መሠረታዊ መርሆዎች!

‹‹The Dynamics of Guerrilla War››

/በፕ/ር፣ ዶ.ር ኤሪክ ሆብስባም እና በፕ/ር ሎረንስ ፍሪድማን እንደተሰናዳው/

የዚህን ጽሑፍ ሀሳቦች ያሰባሰብኩት ራሳቸውም የብዙ ሽምቅ ታጋዮችንና የጦር ጠቢቦችን ሀሳቦች አካትተው በመጽ ሐፍ መልክ ካቀረቡ ሁለት ሰዎች ሥራዎች ነው፡፡ አንደኛው ‹‹LIMITED WAR & DEVELOPING COUNTRIES›› በሚለው፣ ፕ/ር ሎረንስ ፍሪድማን በአርታዒነት ካሠናዱት ዕውቅ ሥራ ውስጥ፣ የማኦን የጦርነት መርሆዎች የቀረቡበት ጽሑፍ ነው፡፡

ሁለተኛው ደግሞ በኤሪክ ሆብስባም የተዘጋጀው ሌላኛው በደፈጣ ውጊያና በአብዮቶች ዙሪያ እንደ ማጣቀሻ (እና በወቅቱ እንደትንቢም) የሚቆጠር እጅግ ታዋቂ መጽሐፍ ነው፡፡ ደራሲው ከመጽሐፉ 5 ክፍሎች አንዱ በሆነው - ‹‹SOLDIERS AND GUERRILLAS›› - በሚለው ውስጥ፣ ‹‹The Dynamics of Guerrilla War›› በሚል ራሱን የቻለ ምዕራፍ ያቀረበውን፣ ስለ ዘመናዊው የደፈጣ ውጊያ ባህርያት፣ ስለማይታጠፉ መርሆዎቹ፣ እና ወጤታማ ስልቶቹ ያቀረበውን በተቻለ መጠን አሳጥሮ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ!

የተለያዩ የደፈጣ ውጊያ ተሞክሮዎችን፣ የታሪክ ድርሳኖችን፣ የጦር ሊቃውንትን ትንታኔዎች፣ እና በታሪክ የታዩ ስኬቶችና እንከኖች እየተነሱ፣ ምሳሌዎች እየተዘረዘሩ ቀርበዋል፡፡ ተተንትነዋል፡፡ ተሞግተዋል፡፡  ብዙ ምክሮችና ማስጠንቀቂያዎችም አሉበት፡፡ እና የትግል ትንበያዎች፡፡ ስለ መፃዒው የህዝቦች ድኅረ-ትግል ዘመን፡፡ በተቻለ መጠን ትንታኔዎቹና ምሳሌዎቹ ሲቀሩ፣ ዋነኛ ሀሳቦቹን ግን ይኸው!  

የደራስያኑ ትንታኔ የሚጀምረው በመደበኛ ጦርነቶች ነው፡፡ በመደበኛ ጦርነቶች ውስጥ፣ ይላል ዶ/ር ሆብስባም - በደፈጣ ውጊያ ስልቶች መድብሉ ላይ - አንድ ሠራዊት ወደ ጦርነት ገብቶ በአሸናፊነት እንዲወጣ የሚያስፈልጉ ሶስት መሠረታዊ ነገሮች አሉ፡፡ በዘመናዊው ዓለም በመደበኛ ጦርነት ድል የሚገኘው፣ ከሶስቱ ቢያንስ አንዱን ባሟላ ወገን ነው፡፡ ሶስቱ የድል ቅመሞች ምንድናቸው?

ለውጊያ የማያመነታ ግዙፍ ህዝብ - አንድ፡፡ 
ማምረት የማይደክመው ግዙፍ የኢንዱስትሪ አቅም - ሁለት፡፡ 
ፍንክች የማይሉ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት - ሶስት፡፡

እነዚህ ሶስቱም ያሉት ተዋጊ በቀላል አነጋገር ‹‹unbeatable›› ነው ይባላል፡፡ ገጥሞ ለማሸነፍ የማይታሰብ! አይነኬ! አይበገሬ! ይሆናል፡፡ ችግሩ ግን - ይላሉ ምሁሩ - ችግሩ ይሄን ያሸናፊነት ቀመር በጊዜ ሂደት ሁሉም አወቀው፡፡ እና ሁሉም የየራሱን ግዙፍ ‹‹ተጠባባቂ ሠራዊት››፣ የጦር ኢንደስትሪ፣ እና ጠንካራ ሲቪል አድሚኒስትሬሽን ለክፉ ቀን አዘጋጀ፡፡ ‹‹ብልጥ ለብልጥ ዓይን ፍጥጥ›› - እንደሚባለው ሆነ፡፡

ዛሬ አንዱ በቴክኖሎጂ ልቆ ቢገኝ፣ ሌላው ደሞ በህዝብ ብዛትና ተጠባባቂ ጦር ብዛት ይበልጣል፡፡ ሌላው ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ ቢኖረው፣ ሌላው ያንን የሚያስከነዳ ቴክኖሎጂ ይኖረዋል፡፡ ሁሉም በየራሱ አንዱ ከሌላው የሚልቅበት የሆነ አድቫንቴጅ ይዞ ይገኛል፡፡ በሁሉም ነገር ፍጹም የበላይነት ያለው፣ በብዙዎች አፍ እንደሚነገረው ያለ ‹‹በጦርነቶች ሁሉ ውስጥ የሚያሸንፍ›› አንድ ‹‹ልዕለ-ኃያል›› ሀገር የለም! ይላሉ እነዚህ ምሁራን!

ታዲያ ሀገሮችም ሆኑ ቡድኖች፣ በመደበኛ ጦርነት ማንም አሸናፊ ወደማይሆንበት እልቂት ውስጥ የሚገባበት ሁኔታን በራሳቸው ላይ ከማስከተል ይልቅ፣ ለምን አማራጭ አዋጪ የጦር ስልት (መፍትሄ) አናዘጋጅም? ወደማለት ገቡ! አንዳንድ ዘመናዊ የጦር ስትራቴጂስቶችም - መፍትሄ ብለው ያቀረቡት - ከመደበኛ ጦርነት ውጭ ያለ - አዲስ ዓይነት የውጊያ ስልትን መቀየስን ነው!

እና ከጥንት ጀምሮ የኖረውን (ነባሩን) የደፈጣ ውጊያ - ከተሞክሮ እና ከመደበኛም ከህዝባዊ ትግሎችም ከተገኙ ልምዶችና የጦር ስልቶች አዋቅረው - አዲስ ዘመናዊ የደፈጣ ውጊያ ስትራቴጂዎችን መንደፍ ጀመሩ፡፡ እነዚህን ጠቅለል ባለ መልክ ስናቀርባቸው፣ በአራት ዋና ጥቅል ሀሳቦች ከፍለን ብናያቸው በቀላሉ ይዘታቸውን ለማግኘት የሚያስችለን ይመስለኛል፡፡

እነዚህ ዘመናዊ የደፈጣ ውጊያን በተመለከተ በምሁራኑ የተዳሰሱት አራት ጥቅል ጉዳዮች ምድናቸው? ያልን እንደሆነ፡- 1ኛው/ ግቡ ነው፡፡ ዘመናዊ ደፈጣ ምን ግቦች አሉት? የሚለው አጭር ነጥብ፡፡ 2ኛው/ ሸማቂ ቡድንን የሚመሠርቱት ምን ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ 3ኛው/ የደፈጣ ተዋጊዎች ሊከተሏቸው የሚገቡ የሥነምግባር መርሆዎች እንደምን ያሉ ናቸው? የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ 4ኛው/ እና የመጨረሻው ደሞ የደፈጣ ተዋጊዎችን የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ምንድናቸው? ምንስ አድርገው ተሻገሯቸው የሚሉት ጉዳዮች ናቸው፡፡ አራቱንም በየተራ አቀርባቸዋለሁ!    

የዘመናዊ ደፈጣ ግቦች ምንድናቸውinbound240453058277886704
?
-------------------------------------

ዘመናዊ የደፈጣ ውጊያ ሁለት ዋነኛ ግቦችን ሊይዝ ይችላል፡፡ አንድም አንድን ኃይል በማያቋርጥ መልክ ‹‹ዕረፍት የመንሣት›› ግብን ያነገበ፡፡ ስለዚህም የተመጠነና ውሱን ወታደራዊ ግቦች ያሉት ሊሆን፡፡ አሊያ ደግሞ ሁሉን-አቀፍ (ብሔራዊ፣ አህጉራዊ ወይም ዓለማቀፋዊ) ግቦችን ያነገበ ሊሆን ይችላል፡፡

የደፈጣ ውጊያ ከእነዚህ መሐል የትኛውንም ዓይነት ግብ ለማሳካት የሚካሄድ ቢሆን፣ ሁልጊዜም በውስጡ፣ ፖለቲካዊ ግቦችን ማነገብ አለበት! ፖለቲካዊ ግብ የሌለው የደፈጣ ውጊያ ዘመናዊ ባህርዩን ያጣል፡፡ ያለፖለቲከ ዓላማ የሚደረግ ደፈጣ በገጠር ከሆነ ተራ ግጭት (‹‹skirmish››) ብቻ፣ በከተማ ከሆነ ደሞ ‹‹ሽብር›› ብቻ ሆኖ ይቀራል! ስለዚህ ዘመናዊው የደፈጣ ውጊያ የፖለቲካ መሣሪያ መሆኑን መገንዘብ እጅግ ጠቃሚ ነው! የፖለቲካ ግቦችን ለማሳካት ተብሎ የሚደረግ ነው! ስለዚህም ዘመናዊው የደፈጣ ትግል፣ የፖለቲካ ኃይሎችም ከተዋጊዎች ጋር ተናበው አስተዋፅዖ የሚያደርጉበት ተያያዥ ትግል ነው!

ዘመናዊ ሸማቂዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው?
-----------------------------------------------

ዘመናዊው የሽምቅ ኃይል የሚጀመረው በሠላማዊ መንገድ ጥያቄያቸው እንደማይስተናገድ ባመኑ ጥቂት ሰዎች አማካይነት ነው፡፡ እነዚያ ጥቂት ሰዎች ጥቂት የፖለቲካዊ ግንዛቤ ያላቸው ወጣቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወይም የ50ና 60 ዓመት ጎልማሶች፡፡ አሊያም የ70 ዓመት አባት አርበኞችም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማንም ይሁን፣ ማንም ይጀምረው፣ ከተጀመረ በኋላ ግን ትግሉ የወጣቶች ነው!

ዘመናዊ የደፈጣ ተዋጊዎች በተቻለ መጠን ከጭቁኑ ህዝብ አብራክ የወጡ (ስለሆነም ብዙ አስቸጋሪ የትግል ምዕራፎችን በጽናት ሊወጡ የሚችሉ)፣ ከተቻለም ደግሞ ከገጠሪቱ የሀገሩ ክፍል የበቀሉ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ ከታሪክ፣ ከልምድ በታየው ነው!

የደፈጣ ተዋጊዎች በተቻለ መጠን የሚዋጉበትን አካባቢ ጋራና ሸንተረር ጠንቅቀው የሚያውቁ የዚያው የሚታገሉለት አካበቢ ሰው መሆን አለባቸው! (ይህ ከመደበኛ ሠራዊት የሚለያቸው፣ እና የአካባቢው ህዝብ ‹‹የኛ ልጆች›› ብሎ እንዲያቅፋቸው የሚያደርግ እሴት ነው!)፡፡

የደፈጣ ተዋጊ ቡድንን የሚመሰርቱ ሰዎች በሥርዓቱ የደረሰባቸው ምሬት፣ ወይም ለሥርዓቱ ያላቸው ተቀናቃኝነት ከፍ ያለና፣ ያም ምሬት ፈጽሞ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ለመጣል ቆራጥ ያደረጋቸው፣ ጠንካራ አቋም ያላቸው፣ የማይደለሉ፣ የማይወናበዱ ሰዎች ናቸው፡፡

በደፈጣ ጅማሮም ሆነ በሂደት የደፈጣ ተዋጊዎች አካላዊም አዕምሯዊም ጥንካሬና ብቃት የተላበሱ ሊሆኑ ግድ ነው፡፡ አካላዊ ቁመናቸው በቀላሉ ከቦተታ ቦታ፣ ዳገትና ቁልቁለት፣ አስቸጋሪ አረንቋና ሰርጦችን፣ አሊያም ወንዝና ኩሬውን ለመሻገር የሚያስችላቸው መሆን ይገባዋል፡፡ ከአሳዳጆቻቸው የበለጠ መከራን የመቋቋም ችሎታ ያላቸው የዚያው አካባቢ ሰዎች ናቸው!

መደበኛ ወታደሮች ምርጥ የአደባባይ ሰልፍ ማድረግን ሊማሩ ይችላሉ፣ መገለባበጥና ጁዶ ሊማሩ ይችላሉ፣ አሊያም ወታደራዊ አለባበሳቸው ያማረና ሥርዓት ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ - ነገር ግን በደፈጣ ውጊያ ወቅት - እነዚህ አንዳቸውም ዋጋ የሌላቸው ነገሮች ናቸው - ይላሉ ምሁራኑ!

የደፈጣ ውጊያ - በመደበኛ ወታደሮች ላይ የሚመጣባቸው - ልክ እንደ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ነው ይላል! የሰልፍ ትርዒታቸው አያድናቸውም፣ አስቀድመው ትክክለኛዋን ቅጽበት አውቀው መገኘት አይችሉም፣ ሲደርስባቸው ሁኔታው ከቁጥጥራቸው ውጭ ነው፣ ፋታ አያገኙም፣ እና ቀጥሎ ምን እንሚሆን አያውቁም (እግዜራቸው ብቻ ነው የሚያውቀው ያንን - ይላል አንዱኛው ደራሲ ቃል-በቃል)!

ስለዚህ ለአንድ የሽምቅ ተዋጊ እጅግ አስፈላጊው ነገር - መከራን የመቋቋም ችሎታ - በተለይ ከልጅነቱ ያደገበት፣ የቦረቀበት፣ ከጢሻው ቀጥፎ የሚበላበት፣ ያካባቢውን ሰው ቢቸገር በሚገባው አመሉ የሚያናግርበት፣ መውጫ መግቢያ አቋራጩን ሁሉ የሚያውቀው፣ የማይቸግረው፣ አካባቢውን ተቋቁሞ ፀንቶ መዝለቅ የሚያስችለው ፅናት ነው የሚያስፈልገው!  የዓላማ ቁርጠኝነት ነው! የአርበኝነት ስሜት ነው!

በተኩስና የመሣሪያ ችሎታም በኩል - ቀላላል መሣሪያዎችን (ጠብመንጃዎችን) መተኮስ ከቻለ ለደፈጣ ተዋጊ በቂው ነው! የግድ ወታደራዊ ስልጠና አያስፈልገውም! የታወቁ ዓለማቀፍ የደፈጣ ተዋጊዎች ‹‹ፕሮፌሽናል›› ወታደሮች አልነበሩም፡፡ (ለምሳሌ እንኳ ቼ ጉቬራ ሃኪም ነበር፡፡ የቬትናሙ ነፃ አውጭ ጄነራል ቮ ንጉዬን ጂያፕ ራሱን በራሱ በልምድ ውትድርና ያስተማረ የጦር አዋቂ ነበር፡፡ ማኦ ዜዶንግ ከተለያዩ ትምህርትቤቶች እያቋረጠ የወጣ ወጣት ነበር፣ ራሱን በራሱ የጦር ስልትን ያስተማረ ነበር፡፡ ሌሎችም ብዙ፡፡

/ከመጻህፍቱ ወጣ ብለን ወደራሳችን ካየንም፣ በዱር በገደል ፋሺስት ጣልያንን መድረሻ ያሳጡ የኢትዮጵያችን አርበኞችም በአብዛኛው ዘመናዊ የጦር ትምህርት የነበራቸው አልነበሩም! ትልቁ ሀብታቸው ለቆሙበት ዓላማ፣ ለሀገራቸው፣ ለህዝባቸው፣ ለትውልድ፣ ለነፃነታቸው፣ እና ከምንም በላይ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ ለመሰዋት የነበራቸው ከፍ ያለ ቁርጠኛ አቋም ነበር!/

በእርግጥ አሁን ደፈጣውን የሚያሳድደው የጠላት ኃይል ቀድሞ አሰልጥኖት የነበረ ወታደር የሽምቅ ቡድኑን ከተቀላቀለ በብዙ መልኩ በበጎ ጎኑ መበረታታት አለበት - ይላል ደራሲው! ምሳሌዎችን በየዓለም ማዕዘኑ ከተካሄዱ የጎሪላ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚጠቀሱ ተሞክሮዎችን እያስታወሰ! እነዚህ ከራስ ወገን የሆኑ ስልጡን ወታደሮች የሚያስፈልጉት - ለመጨረሻው - ደፈጣው ወደ ሙሉ ‹‹ሠራዊት›› አድጎ - በግልጽ አውደውጊያ - መደበኛውን ጦር ለሚገጥምበት ጊዜ ነው!

ወደ ደፈጣው አዳዲስ የሚቀላቀሉ ተዋጊዎች ከሌሎች አካላዊና የጦር ስልጠናዎች በተጨማሪ - የፖለቲካዊ ንቃታቸው ከፍ እንዲል - ዘወትር የጓደኛ ለጓደኛ ዓይነት የግንዛቤ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል! ስለሆነም ዝግጅታቸው አካላዊም፣ አዕምሯዊም ይሆናል! በቀላሉ በሌሎች ተቃራኒ ቡድኖች አይማረኩም፣ አይወናበዱም! ከራሳቸው አልፈው ለህዝብና ለሀገር መቆማቸውን ያውቃሉ! ከፍ ያለ የሞራል ስንቅ ይሆናቸዋል!  

በሰፊ ግዛት ላይ ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ ትናንሽ የደፈጣ ተዋጊ ቡድኖች ልክ በተለያየ ቅርጽና ቁመና ለሰውነታችን አገልግሎት የሚሰጡ የሰውነቶቻችንን አካላት አድርገን ልንመስላቸው እንችላለን፡፡ የደፈጣ ውጊያ አድጎ ሀገራዊ (ብሔራዊ) ይዘትና ግብ ተላብሶ በሚቆምበት ወቅት ላይ - አንዱን የአካል ክፍል ከሌላው የአካል ክፍል ጋር የሚያስተባብሩ፣ የሚያስተሳስሩ፣ ኒውክለሶች፣ እና የሚያገናኙ፣ መረጃና አሰላለፉን የሚያቀናጁ የደም ሥሮችና የአንጎል ክፍል ያስፈልጋቸዋል፡፡

ስለሆነም፣ በተለይ በተለይ፣ የደፈጣ ውጊያዎች እየተጠናከሩና የጉልበተኛውን መንፈግሥት ዋና ጉልበት ያረፈባቸውን የልብ ትርታዎቹን ወደማጥቃት ደረጃ በሚሸጋገርበት ወቅት - በአንድ አካባቢ ያሉ የደፈጣ ተዋጊዎች ከሌሎች ጋር ለጋራ ኦፕሬሽን የሚረዳዱበት የግንኙነት መስመር፣ እና የፖለቲካ ቁርኝት ሊኖራቸው የግድ ይላል! ለዚህ ተግባር ደግሞ በተለይ በቂ የፖለቲካ ግንዛቤው ያላቸው (ልክ እንደ ካድሬ ሆነው የሚያገለግሉ) የህዝቡ ልጆች ከተዋጊዎቹ መካከል በጥንቃቄ ተመርጠው የአጠቃላዩን የሀገራዊውን እንቅስቃሴ ሊያስተባብሩ ይገባል፡፡

እነዚህ አባላት ናቸው - ትግሉን ከደፈጣ ተዋጊዎቹ አሻግረው ለሀገሪቱ ህዝብና የፖለቲካ ቡድኖች (ፓርቲዎች) የሚሰጡትና አጋር የሚያበጁት! እነዚህ አባላትም ናቸው የፖለቲካ የጀርባ አጥንት ሆነው ለሰፊው ሀገራቀፍና ዓለማቀፍ ደጋፊ የህዝብ ግንኙነት ድልድይ ሆነው የሚሰሩት!

ስለዚህ በጅማሬውም ባይሆን በሂደት የደፈጣ ውጊያ እነዚህን ሰዎች ሊያቅፍ የግድ ይላል፡፡ በትግል ሂደት እንደታየው የከተማ ሰዎች፣ የተማሩ፣ ለደፈጣ የሚሆን ከፍተኛ የትግል ጽናት በብዛት ባይገኝባቸውም፣ ለእነዚህ ተግባራት ግን በጽናታቸው ተፈትነው የታዩ እነዚህን መሰል ታማኝ ታጋዮች ለዚህ ተግባር መመልመልና መዘጋጀት አለባቸው!

ዘመናዊ የደፈጣ ተዋጊዎች ሊከተሏቸው የሚገቡ የሥነምግባር መርሆዎች!
-------------------------------------------------------------------------------
ማኦም፣ ቮ ንጉዬን ጂያፕም፣ ቼ ጉቬራም - የየራሳቸውን የደፈጣ ውጊያ መመሪያዎች የጻፉና ዕድሜያቸውን ለደፈጣ ትግል አሳልፈው የሰጡ ሰዎች ናቸው፡፡ በሶስቱም መመሪያዎች ውስጥ የሚገኙ (እና ከተጣሱ ኋላ መልሰው ለደፈጣ ቡድኑ ጠንቅ የሚሆኑ) መሠረታዊ የሥነምግባር መመሪያዎች አሉ፡፡

በማንኛውም ሁኔታ፣ የደፈጣ ተዋጊ ከሚንቀሳቀስበት አካባቢ ህዝብ፣ በጉልበት የሚጠይቀው ትብብር፣ በነጻም እንደራሱ ጓዳ በፈቃዱ ዘግኖ የሚወስደው አገልግሎት አይኖርም!    

የደፈጣ ተዋጊ ከያካባቢው ህዝብ ለሚቀበለው አገልግሎት ሁሉ በተቻለው መጠን ተመጣጣኙን ዋጋ ይከፍላል፡፡ አሊያም ሁኔታው አመቺ በሚሆንበት ጊዜ ለመክፈል እንዲያመች መዝግብ አደራጅቶ ማቆየት አለበት፡፡ /ይህ ማስረጃ በጠላት እጅ ከገባ ለደህንነታቸው አስጊ ሲሆን፣ በደፈጣው ውስጥ ያለ የያካባቢው ሰው፣ እና የቡድኑ መሪዎች ከህዝቡ የተገኙትን አገልግሎቶች እንዲያውቋቸው መደረግ አለበት!

በማንኛውም ወቅት፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ፣ የደፈጣ ተዋጊ፣ የአካባቢውን ሴቶች አስገድዶ በመድፈር ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ መገኘት የለበትም! ከተገኘ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድበት ሁሉም የደፈጣ አባል አስቀድሞ ሊያውቀው ይገባል!

የደፈጣ ተዋጊ፣ በፍጹም፣ እና በምንም ዓይነት አጋጣሚ፣ ከአካባቢው ህዝብ የተለየ የቅንጦት አለባበስ ለብሶ አይገኝም! ከአካባቢው ህዝብ ኑሮ የተለየ የቅንጦት አዋዋል ሊኖረው አይችልም! በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ፣ የደፈጣ ተዋጊ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር አንድና ተመሳሳይ ዓይነት የዕለት ኑሮን መግፋት አለበት!

የደፈጣ ተዋጊዎች በሚያልፉበት አካባቢ ሁሉ፣ ያልታረሱ መሬቶችን ለነዋሪው ማከፋፈል አለባቸው! በእርሻ ወቅት ገበሬውን መርዳት አለባቸው! በሥርዓት በሚመራና ስምምነት በተደረሰበት መንገድ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የሚፈጠሩ የፍትህ መዛባቶችን ለማረም፣ ፍትህን ለማስፈን፣ ሚዛንን ለማስተካከል፣ የህዝቡን ሀቅ ለመመለስ ወደኋላ ማለት የለባቸውም! የደፈጣ ተዋጊዎች በሚያልፉበት አካባቢ ሁሉ፣ ጊዜና ሁኔታ በፈቀደ መጠን ትምህርትን ማስፋፋትና ቢያንስ የመማሪያ ዳሶችን ለህብረተሰቡ ልጆች እያቆሙ መሄድ አለባቸው!

ትልቁን ዓላማና ግባቸውን ለህብረተሰቡ ከማስረዳት ባለፈ፣ የደፈጣ ኦፕሬሽኖችን ከቡድኑ ውጭ ላለ ሰው ማጋራት ፍጹም ክልክል ነው! በመንግሥት ኃይሎች የሽብርና የማሰቃየት ተግባር የተነሳ፣ የደፈጣ ተዋጊዎቹን አቅጣጫና መረጃዎች ለጠላት አሳልፈው የሰጡ የህብረተሰቡ አካላት ቢኖሩ፣ የደፈጣ ተዋጊዎች የበቀል እርምጃዎችን አይወስዱም! በምክርና ማስጠንቀቂያ፣ በከፍተኛ ትዕግሥት ማለፍ አለባቸው!

የደፈጣ ተዋጊዎች እንቅስቃሴያቸውን ሁሉ ድንገተኛና ተገማች ያልሆነ ማድረግ አለባቸው! የደፈጣ አባላት፣ ለስትራቴጂክ ጠቀሜታ ሲባል ያሉበትን ቀጠና ሊናገሩ ካልቻሉ በቀር፣ የተለየ መገኛ አድራሻቸውንም ሆነ ዝርዝር ዕቅዶቻቸውን በፍጹም ማጋራት የለባቸውም! (ይሄ በመደበኛ ሠራዊቶች ውስጥ ‹‹ምሥጢር የመጠበቅ ቃልኪዳን›› የሚባለውና በህይወት ጭምር የሚጠበቅ ነው፣ በደፈጣዎች ዘንድ ደግሞ ከዚያም በበለጠ መስዋዕትነት መጠበቅ አለበት!)

የደፈጣ ተዋጊዎች በሚፈለጉና በተመረጡ የአውራጃ (ከከተማ ውጭ ያሉ) አካባቢዎች ላይ የመደበኛውን ወታደራዊ ኃይል እንቅስቃሴዎች ለማስተጓጎልና ለማወክ፣ የየአከባቢው ሲቪል ህብረተሰብ መንገዶችን በመዝጋት እንዲተባበራቸው የህዝብን እርዳታ መጠየቅ (ግድ ማለት) ይችላሉ! በተቻለ መጠን ህዝቡ ለእርሱ የቆሙለት መሆናቸውን አምኖ፣ በራሱ ተነሳሽነት እነዚህን ቁልፍ ተግባራት እንዲፈጽማቸው ለማሳመን መሥራት አለባቸው፡፡ ነገር ግን በጥያቄያቸው በሚፈጸሙ ድርጊቶች ሁሉ የደፈጣ ተዋጊዎቹ ኃላፊነቱን ራሳቸው መውሰድ አለባቸው! ይህም የአካባቢውን ሰላማዊ ነዋሪ ከሠራዊቶች የበቀል እርምጃ ለመጠበቅ ይረዳል!

የደፈጣ ተዋጊዎች ከህዝቡ ጋር መቀላቀል ይችላሉ! ተዋጊ የሆኑትንና ተዋጊ ያልሆኑትን ዒላማዎች መለየት የተሳነው ወራሪው ኃይል በአጠቃላይ ህዝቡ ላይ የጅምላ ጥቃት ከፈጸመ - መቀበሪያ ጉድጓዱን ቆፈረ ማለት ነው! ወደ ደፈጣ የሚቀላቀሉ ብዛት ያላቸው ሰዎች ጎርፈው የሚገኙትም የዚህ መሰል ጅምላ ጥቃት ሰለባ ከሆኑ አካባቢዎች ነው! ነገር ግን የደፈጣ ተዋጊዎች ሌሎች አማራጮች እያሏቸው ሆነ ብለው - አሊያም እንደ ታክቲክ - ሰላማዊ ሰዎችን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ መጠቀም የለባቸውም!

በደፈጣ ተዋጊዎች መካከል ወንድማማችነትና ቤተሰባዊነት መገንባት አለበት፡፡ አብሮ መከራን መካፈል፣ አብሮ ለጋራ ዓላማ መቆም፣ አብሮ ካንድ አካባቢ መውጣት፣ አብሮ ድልንም ሆነ ሽንፈትን ማጣጣም የሚሰጠው የመንፈስ አንድነትና ጥንካሬ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የደፈጣ ቡድኖች፣ በሌሎች ሠራዊቶች ላይ ጦሩን ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ በማለት የሚደረጉ እርስበርሱ በጎሪጥ የማስተያየትና የመከፋፈል ድርጊቶች በፍጹም መደረግ የለባቸውም! የደፈጣ ቡድን ዋነኛ የጥንካሬ ምንጩ በትግሉ ሂደት የሚፈጠው ጥብቅ ቤተሰባዊ ቁርኝቱ ነው!

የደፈጣ ተዋጊ የቆመለትንና የሚዋጋለትን ህብረተሰብ በጥቅም አይደልልም! የተጨቆነ ህዝብ የሚፈልገው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ብቻ አይደለም! ዳቦ ብቻ አይደለም! መሬት ብቻ አይደለም! ከዚያ በላይ የሆነ ነጻነትን ነው የሚፈልገው! የተበደለው በደል እንዲሰረዝለት ነው የሚፈልገው! ጭቆናው እንዲወገድለት ነው የሚፈልገው! በሠላም ደረቱን ነፍቶ መኖር ነው የሚፈልገው! ግፈኞች ከላዩ እንዲነቀሉ፣ ግፈኛ ሥርዓት እንዲወገድለት ነው የሚፈልገው! ይሄ ነው የደፈጣ ውጊያ ዋነኛ ፖለቲካዊ ግቡ! እንጂ ጊዜያዊና አላፊ ጥቅሞች አይደሉም! ስለሆነም፣ የደፈጣ ተዋጊ በእነዚህ ጥቅሞች ህዝብን መደለል መከልከል አለበት!

የደፈጣ ቡድን - በተለይ የከተማ ደፈጣ ቡድን - ዋነኛ ሥራው መንግሥትን ወይም የጉልበተኛውን ሠራዊት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት ማሸበር ነው፡፡ የማያቋርጥ ስጋት መደቀን ነው፡፡ የተሸበረ መንግሥት ራሱን ከጥቃት ለመከላከል በገጠር ሊያሰማራው ይችል ከነበረው በርካታ ሠራዊቱን ቀንሶ፣ ከተሞቹንና የራሱን ተቋማት ለመጠበቅ ያውላቸዋል! ይህ ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የሚካሄደውን የደፈጣ ትግል በተዘዋዋሪ ያግዘዋል! የከተማ ደፈጣ መንግሥትን ማሸበር ሥራው ቢሆንም፣ ነገር ግን በምንም ዓይነት የቆመለትን ህብረተሰብ፣ ሠላማዊ ሕዝብን፣ እና ሌላ ቀርቶ የሚቃወመውንና ያላቀፈውን ህብረተሰብ ማሸበር የለበትም!

የደፈጣ ተዋጊ ቡድኖች በጊዜያዊነትም (ለአንድ ወይም ለጥቂት ተግባር) አሊያም በቋሚነት የመለመሉትን አባል ማንነት በምስጢር የማቆየት (ማንነቱን፣ ስሙን፣ ቤተሰቦቹን፣ የመጣበትን ሥፍራ፣ ለቡድኑ ያበረከተውን ሚና፣ ወዘተ በከፍተኛ ምስጢርነት የመጠበቅ) በጊዜ የማይገደብ ግዴታ አለባቸው! የቅስቀሳ ፎቶግራፎች፣ ፖስተሮችና በራሪ ጽሑፎች ለህዝብ ሲሰራጩ - በውስጡ የሚጠቀሱ ስሞች ካሉ - ሁልጊዜም የባለቤቱ ፈቃድ መጠየቅ አለበት! ሁልጊዜም ከቡድኑ ደህንነትና ከሚያስከትለው አሉታዊ ጉዳት አንጻር መፈተሸ አለበት!

የደፈጣ ተዋጊ የአካባቢውን ህብረተሰብ ባህል፣ አኗኗር፣ ትውፊት፣ ሥርዓትና (ሐይማኖትም ቢሆን) አክብሮ መንቀሳቀስ አለበት፡፡ የፖለቲካ ግቦች ለአንድ ህብረተሰብ እንዲሰርፁ ሲደረጉ፣ በተቻለ መጠን፣ ከራሱ ከሚያምንበት ባህልና እምነት ጋር አብሮ እንዲሄድ ተደርጎ መነገር አለባቸው! በምንም ዓይነት መንገድ የህብረተሰቡ የአምልኮ ስፍራዎች የደፈጣ ተዋጊዎች ቀጥታ ተቃውሞም፣ ትችትም፣ ጥቃትም ሊደርስባቸው አይገባም! የደፈጣ ተዋጊዎች ለህብረተሰቡ ስነልቡና፣ ባህልና ሥርዓት ከፍተኛ አክብሮት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል! የደፈጣ ተዋጊዎች ከራሱ ከዚያው ከሚታገሉለት አካባቢ የተውጠጡ ቢሆኑም የሚመረጥበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው!

ትናንሽ የደፈጣ ተዋጊዎች፣ በጊዜ ሂደት ግዙፍና ቋሚ ቦታ ይዞ ፊት ለፊት የሚዋጋ ሠራዊት እስኪያደራጁ ድረስ፣ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ያሉትን የገዢውን መንግሥት መዋቅሮችና ለወደፊት ጥቃት የሚውሉ መሠረተ ልማቶች የማውደም ተግባር ቢፈጽሙም፣ የየአካባቢዎቹን ሲቪል አስተዳደሮች ግን በራሳቸው የመተካትን ሥራ ማቆየት አለባቸው! እነዚህን የራስ አስተዳደሮችን የማዋቀርና የመትከል ሥራዎች የደፈጣ ትግሉ ወደ መደበኛ ሠራዊት ትግል ከፍ በሚልበት ጊዜ የሚፈጸም ስለሆነ፣ በተቻለ መጠን የየሥፍራውን የሲቪል አስተዳደሮች ባሉበት ሁኔታ መተው ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ አለው!
 
ዘመናዊ የደፈጣ ተዋጊዎች ሊሻገሯቸው የሚገቡ ዋነኛ የአስተሳሰብ ተግዳሮቶች!
-------------------------------------------------------------------------------
የደፈጣ ውጊያ ሁሉም ቦታ በአንድ ዓይነት የሚሠራ ፎርሙላ የለውም፡፡ ለአንድ ተመሣሣይ በሽታ አንድ ቁርጡ የታወቀ መድኃኒት እንደሚታዘዘው ዓይነት አይደለም! የሽምቅ ትግል በአንድ ሀገር ውስጥ፣ በአንድ ክልል ውስጥም እየተካሄደ፣ እንደየቦታው፣ እንደየሰዓቱ፣ እንደአመቺነቱ፣ እና እንደየተሰለፈው ጠላት ዓይነትና ጠባይ ላይ ተመስርቶ፣ አስር ሺህ ዓይነት የየራሱን ስልቶች የሚከተል - እጅግ ፈጠራ የታከለበት - ዘርፈ ብዙ የተናጠል እርምጃዎችና ስልቶች የሚተገበሩበት - ትግል ነው! ስለሆነም የደፈጣ ተዋጊዎች ለሁሉም ቦታ የሚሠራ አንድ ዓይነት የትግል ቀመር ለመፈለግ መባዘን የለባቸውም! አስር ሺህ ዓይነት የማጥቂያና የመከላከያ ዘዴዎችን መፈልፈል ያስፈልጋል!

የደፈጣ ውጊያ (በተለይ ቀጣናው እየሰፋ ሲመጣ) በውስጡ የተለያየ ፍላጎት፣ የተለያየ ብሔር፣ የተለያየ ሐይማኖት፣ የተለያየ የኑሮ ደረጃና አመለካከት፣ የተለያየ ቋንቋ ጭምር ያላቸው፣ የተለያዩ ሰዎች የሚሳተፉበት ነጻነትን ለህዝብ ለማቀዳጀት ከጉልበተኛ ወራሪ ሠራዊት ጋር የሚደረግ የጋራ ስልታዊ ትግል ነው! በዚህ ወስጥ የተለያዩ የአመለካከት፣ የስልት፣ የዘር የጎሳ የአውራጃ ልዩነቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ልዩነቶች የደፈጣውን አድማስ በአካባቢና በጎጥ ወይም ወደ አንድ ህዝብ ብቻ ደረጃ ሊያሳንሱትና ሊከፋፍሉት ይችላሉ! ከዚህም በላይ ትግሉን ለማኮላሸት ለተሠማሩት ኃይሎች ፈጣን የመግቢያ ቀዳዳ ይፈጥሩላቸዋል፡፡ ይህ በሚያጋጥምበት ጊዜ፣ በፍጥነትና ከሥር ከሥር ልዩነቶችን እያቻቻሉ የጋራ ግንባር ለመፍጠር፣ በጋራ ጠላት ላይ ለማተኮር፣ እና ደፈጣዎቹ እርስበርስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስለሚተጋገዙበት መንገድ አዳዲስ መንገድ ለመፍጠር ሳይታክቱና ሳይዘናጉ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል!

የደፈጣ ውጊያ ከኖርማል ኑሯቸው ወጥተው የህዝብን ትግል የተቀላቀሉ ሰዎች የሚያካሂዱት ትግል እንደመሆኑ፣ ልምድ የሌላቸው ሰዎች፣ በቂ የፖለቲካ ንቃት ያላዳበሩ፣ የተለያዩ የጠላትን የማታለያ ታክቲኮች በተገቢው መጠን ለመረዳት በቂ ልምድና ግንዛቤው የሌላቸው፣ ወኔና ቁጭታቸውን ብቻ ይዘው የሚቀላቀሉ አባላት መብዛታቸው አይቀርም፡፡ ሸማቂዎች በአብዛኛው ከግዙፍ ኃይል ጉያ ሥር ሆነው፣ በስውርና በጥበብ የሚንቀሳቀሱ መሆን ስለሚጠበቅባቸው፣ በደፈጣ ወቅት ልምድ በሌላቸው ጥቂት አባላት ስህተት ምክንያት፣ ከባድ ዋጋ የሚከፈልበት ጊዜ ይኖራል፡፡ እነዚህን ዓይነት ሰዎችና አጋጣሚዎች አስቀድሞ አውቆ፣ በተለይ ከአካባቢያቸው ራቅ ላሉ የደፈጣ ኦፕሬሽኖች ልምድ የሌላቸውን ሰዎች ከማሰማራት በፊት፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ በደፈጣ ውስጥ ትዕግሥት ባጡና በተወናበዱ ሰዎች የተነሳ የሚከሰቱ ውስጣዊ ግርግሮችና ግጭቶች (አለመግባባቶች) እንዳይኖሩም ሁልጊዜም እያረጋገጡ መጓዝ የግድ ይላል!

የደፈጣ ተዋጊዎች ቁጥር ወይም አቅም - ከሚጋፈጡት ግዙፍ ጠላት ጋር ሲነጻፀር ድልን ለመቀዳጀት እጅግ አቅመ-ቢስ፣ ወይም ውሱን ሆኖ ሊገኝ ይችላል! በሌላም በኩል የደፈጣ ተዋጊዎቹ የቆሙለት ህዝብ ካሸነፈ ለኛም አይመለስም ብለው የሚያስቡ የቅርብና የሩቅ ጎረቤት ኃይሎች ካሉ - በጋራ በመጣመር - ሸማቂዎቹ የሚታገሉለትን ህዝብ አቅም ኢምንት ሆኖ እንዲገኝ የሚያደርጉበት አጋጣሚ አይታጣም (ለምሳሌ የኩርድ ሸማቂዎችን ተመልከት)! ይህ ዓይነቱ ትንሽነት በሚያጋጥምበት ጊዜ ከሌሎች ውጫዊ ኃይሎች እርዳታ የሚገኝበትን መላ መፍጠር፣ ብዙ ህዝብ ትግሉን የሚቀላቀልበትን ሰፋ ያለ ግብ መፍጠር፣ እና ወራሪው እውነተኛ ጭራቃዊ ማንነቱ ለሁሉም በግላጭ እንዲታይ የሚያደርጉ ስልታዊ እርምጃዎችን መውሰድ ጠቃሚ ይሆናል!

የከተማ የደፈጣ ትግል - በታሪክ በተዳጋጋሚ ጊዜ ተሞክሮ የሚከሽፍ፣ ነገር ግን ብዙ መስዋዕትነትና ደም መፋሰስ የሚያስከትል ትግል ነው፡፡ የኮሙኒስት ሸማቂዎች በሻንጋይና በካንተን (ቻይና)፣ የፓሪስ አማፂዎች በፈረንሣይ፣ የሚላንና የቱሪን ሸማቂዎች በጣልያን፣ የፖላንድ ሸማቂዎች በዋርሶ፣ የስፔን ሸማቂዎች በባርሴሎና፣ ሌሎችም ብዙ ብዙ አሳዛኝ ምሳሌዎች አሉ፡፡ በብዙዎቹ ሥፍራ ከተሞቹ ለአሸማቂዎች ከመመቸት ይልቅ በመደበኛ የግንኙነትና የስምሪት መስመሮች እንደልቡ ለሚጠቀመው ለወራሪው (ጉልበተኛው መንግሥት) ሠራዊት የተመቹ ሆነው ይገኛሉ፡፡

ስለሆነም፣ የደፈጣ ትግሉ አድጎ፣ እና የደፈጣ ቡድኖች ተሰባስበው ግዙፍ መደበኛ የሠራዊት ቅርፅ ይዘው ካልተገኙ በስተቀር፣ አሊያም ከተሞቹ የሚገኙት ከማዕከላዊው መንግሥት በጣም ርቀው ካልሆነ በስተቀር፣ ከተሞች ላይ የሰፈሩ የወራሪውን ሠራዊትና ኢንፍራስትራክቸሮቹን በድንገተኛ የደፈጣ ማዕበል በተመረጡ ዒላማዎች ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ፣ ከተሞቹን በእጃቸው የማስገባት ዕድሉ የተመቻቸላቸው ቢሆንም፣ ኦፕሬሽናቸው እንደተጠናቀቀ የደፈጣ ተዋጊዎቹ ከተሞቹን ለቀው መውጣት አለባቸው!

መደበኛ ኃይል በሚያደረጁበት ጊዜ ግን - ይህ የደፈጣ ወሰን - ቁርጡና ዋናው የትግሉ መፈተኛ ምዕራፍ ይሆናል! ከዚህ ወሰን በላይ ለመሄድ ይቻላል? ወይስ አይቻልም? ይሄን የሚወስነው - የደፈጣው ትግል የሚደግፈው ህዝብ ስፋት፣ የሀገራዊ ፖለቲካዊ ዓላማው አካታችነት፣ እና ያጠራቀመው መደበኛ ውጊያን ማከናወን የሚችል በቂ የደፈጣ ኃይል የመኖርና ያለመኖር ጉዳዮች ይሆናሉ!

በአጠቃላይ፣ እነዚህን ተግዳሮቶች የተሻገሩ፣ አብዛኛውን የገጠር ወረዳዎች በሀገር ወይም ስፋት ባለው የሀገሪቱ ክልል ደረጃ በቁጥጥራቸው ሥር ያስገቡ፣ የጉልበተኛውን መንግሥት የሲቪል አስተዳደር ከያካባቢው አፈራርሰው ያባረሩ/ያስወገዱ፣ እና መደበኛ የሆኑ የመንግሥቱን የጥቃት መጠቀሚያ መሣሪያዎችና የሰው ኃይሎች በቁጥጥራቸው ሥር ያዋሉ የደፈጣ ተዋጊዎች - በጉልበተኛው ሠራዊት የመሸነፍ ዕድላቸው በመቶኛ ሲሰላ - 0% (ዜሮ ፐርሰንት!) ነው፡፡ ዜሮ ፐርሰንት!

የደፈጣ ተዋጊዎች በዚህ ሀገራዊ ቁመና ላይ ሲደርሱ - ወራሪው ኃይል እፍ ቢሉት የመውደቂያ ጊዜው ደረሰ ማለት ነው! እንደበሰለ ሙዝ ወይም ማንጎ - ረዥም ሸንበቆ አዘጋጅቶ - መውጊያውን አሰናድቶ - በትክክለኛዋ ቦታ ላይ - በትክክለኛዋ ጊዜ - ባለበት ከተማ ሄደው - ነካ ቢያደርጉት - ሙክክ ብሎ በስሏልና - በስብሷልና - ይወድቃል! የመጨረሻው ምዕራፍ - የትግሉ ሁሉ ግብም ተጠናቀቀ ማለት ነው!

ይህ የማይሳካ ተምኔታዊ (ማለትም በህልም የሚቀር) ሩቅ ግብ አይደለም! ይህ በህዝብ ድል አድራጊነት የሚጠናቀቅ መጀመሪያውና መድረሻው የሚታወቅ የህዝብ ትግል ነው፡፡ የደፈጣ ታሪኮች ሁሉ የሚያስረዱት ሀቅ፣ ግዙፎች በትንንሾች እንደሚወድቁ ነው! ከአንዴም ሁለት ሶስቴ፣ ሺህ ጊዜ፣ ብዙ ጎልያዶች በዳዊቶች ሲዘረሩ ታይተዋል! የቆረጠ ህዝብ የራሱ ተዓምር አለው!

ወንድሜ! ከተነሳህ በከንቱ ደመ-ከልብ ሆነህ ለመቅረት አትነሳ! ለታላቅ ህዝባዊ ዓላማ ተነስ! የማትቋቋመውን በደል ከሥሩ ለመንቀል ተነስ! ከሁሉ የሚበልጠውን ነፃነትህን ማንኛውንም ዋጋ ከፍለህ ለመቀዳጀት ተነስ! እስከ ፍፃሜህ ለመዝለቅ ቆርጠህ ተነስ! ጠጠርም ብትወረውር ለውጥ እንዳላት አምነህ ተነስ! እንደ ትንሹ ዳዊት ወንጭፍህን ያዝና ህዝብህን ተቀላቀል! ዳዊትን ሁን! ያንተ ጠጠር ዋጋ አላት! እውነተኛው የማያዳግም ድልም የህዝብ ነው!

ደራስያኑን ሊቃውንት፣ እና ትዕግሥተኛውን አንባቢ፣ ከልብ አመስግኜ አበቃሁ፡፡

ጎልያዶች ይወድቃሉ! የመጨረሻው ድል የተዘበተበት፣ የተረገጠው ህዝብ ነው! ያለምንም ጥርጥር!

የፈጣሪ ብርታት፣ ከእኛ ጋር ይሁን!

ድል ለነበልባሉ ፋኖ!!!

መልካም ጊዜ!!›› እየተባለ የሚጠራውን ይሄን የደፈጣ ውጊያ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ200 ዓመት በፊት ‹‹ጎሪላ›› ብለው የሰየሙት ስፓኒሾች ናቸው፡፡ ትርጉሙም ‹‹ትንሽ ጦርነት›› ማለት ነው፡፡

በኃያሉ የፈረንሣዮች (የናፖሊዮን) ሠራዊት የተወረሩት ስፔኖች፣ በፊት ለፊት ከመጋፈጥ ይልቅ ከ4 ሰው እስከ 20 ሰው የሚደርስ አባላት ያሉት፣ መዓት ተወርዋሪ የደፈጣ ቡድን በማቋቋም፣ እያደቡ፣ እና እግር በእግር እየተከታተሉ፣ በናፖሊዮን ጦር ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀመሩ፡፡

እነዚያ ጥቃቶች ትልቅ ጦርነት አይደሉም፡፡ ጥቃቅን ጥቃቶች ናቸው፡፡ ትልቅን ዝሆን፣ ጥቂት በጥቂት እየገመጥክ በልተህ እንደመጨረስ ማለት ነው፡፡ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ግን ጠላትን እረፍት ይነሳል፡፡ አላፈናፍን ትለዋለህ፡፡ ታዳክመዋለህ፡፡ እና በመጨረሻ ጨርሰህ ትበላዋለህ፡፡

በዚህ ዓይነት መንገድ ስፓኒሾች ሀገራቸውን ከወረራ ነጻ አውጥተዋል፡፡ በሌላ መገዛትን በጄ የማይሉት ጀርመኖችም ተመሳሳይ መንገድ ተጠቅመው ናፖሊዮንን ካገራቸው አባረዋል፡፡ በመሆኑም፣ በአውሮፓ የደፈጣ ውጊያ ከፅንሰቱ ጀምሮ፣ ለነፃነት ከሚደረግ ውጊያ ጋር የተያያዘ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡ የሽምቅ ውጊያ በሀገሮች መካከል የሚደረግ ውጊያ አይደለም፡፡ በግዞት የተያዘ ህዝብ፣ በጉልበት የተወረረ ህዝብ፣ በጉልበተኛው መንግሥት ሠራዊት ላይ የሚያደርገው የነጻነት ውጊያ ነው፡፡

የምዕራቡን ዓለም ዘመናዊ የውጊያ መርሆዎች ቀምሮ ያስቀመጠላቸው፣ እንደሚታወቀው፣ ካርል ቮን ክላውሶቪች ነው፡፡ ክላውሶቪች በእርግጥ ስለ ሽምቅ ውጊያ እንደ መደበኛ ውጊያዎች ብዙ ትንታኔን አያቀርብም፡፡ ነገር ግን ሽምቅ ውጊያንም በሁሉም ባህርዮቹ የተነሳ፣ ጦርነት ነው ይለዋል፡፡ የጦርነት ስልት ነው - ነው የሚለው ክላውሶቪች፡፡

‹‹የሽምቅ ውጊያ፣ እንደ ማንኛውም ጦርነት፣ የፖለቲካ ግብን
ማሳኪያ መንገድ ነው፡፡ ሸማቂዎች በቃልና በእምቢታ የገለጹትን
የፖለቲካ ፍላጎት፣ ከፍ ወዳለ ጠንካራ ቋንቋ በማሻገር፣ ገዢውን
የሚያናግሩበት፣ ቅልብጭ ያሉ የፖለቲካ ግቦች ያሉት፣ እና
የደፈጣውን ውጊያ የሚያካሂዱበት የጠራ ስትራቴጂ የሚይዙበት
ፖለቲካዊ አቋምን የማራመጃ ዓይነተኛ መሣሪያ ነው፡፡››
   — ኦቶ ቮን ክላውሶቪች፣ የጦርነት መርሆዎች

በማለት ይገልጸዋል ክላውሶቪች የሽምቅ ውጊያን ምንነት ሲያስረዳ፡፡ በክላውሶቪች ትንታኔ መሠረት ‹‹የሽምቅ ውጊያ›› ዓለም ከሚያውቀው ‹‹ጦርነት›› ከሚባለው ነገር የሚለየው ሁለት ነገር ብቻ ነው፡፡ መጠኑ፡፡ እና የተዋጊዎቹ ማንነት፡፡

ክላውሶቪች ‹‹መጠኑ›› (‹‹ስኬል››) ሲል የሽምቅ ውጊያ ተዋጊዎቹ ያላቸውን ኃይል ሁሉ አሰባስበው የሚፋለሙበት፣ እና ከፍልሚያው አሸናፊ የሚወጣበት፣ ግዙፍ (ወይም ዋና) ጦርነት አይደለም! ትናንሽ ጦርነቶች ናቸው፡፡ ዓላማቸውም ጠላትን በመጨረሻው ጦርነት ላይ በሚሸነፍበት የጦርነት ቁመና ላይ እንዲገኝ ማሽመድመድ ነው! አካሎቹን መቆራረጥ ነው! ስለዚህ በመጠኑ ከመደበኛ ጦርነቶች ይለያል!        

ሌላው ሽምቅ ውጊያን ከመደበኛ ጦርነቶች የሚለየው የተዋጊዎቹ ማንነት ነው፡፡ እንደ ክላውሶቪች ትንታኔ ‹‹ጦርነት የሚካሄደው በሁለት ሉዓላዊ መንግሥቶች መካከል ነው››፡፡ ጦርነት ማለት ልዩነታቸውን በሠላም መፍታትና ማቻቻል ያልቻሉ መንግሥቶች ልዩነታቸውን ለመፍታት የሚያደርጉት የኃይል ፍጭት ነው! ሽምቅ ውጊያስ? ሽምቅ ውጊያ ግን የሚካሄደው በህዝብ እና በመንግሥት መካከል ነው፡፡

ይህ የሽምቅ ተዋጊዎቹ ማንነት በእርግጥ - ይላል ክላውሶቪች - የጦርነት ህግ በሸማቂዎቹ ላይ የማይሰራበት ዋናው ምክንያት ነው፡፡ ይህ ማለት - አሸማቂዎች በጦርነት ወቅት የተከለከሉ ‹‹መደበኛ ያልሆኑ ዘዴዎችን›› ከመጠቀም የሚከለክላቸው የለም፡፡ የጠላትን ዩኒፎርም ለብሰው ማታለል ይችላሉ፡፡ ማንነታቸውን ሰውረው ከሲቪሊያን ጋር ተመሳስለው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ጦርነት ባልታወጀበትና ‹‹ሆስቲሊቲ›› ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ፣ ሽምቅ ተዋጊዎች አድፍጠው ከባድ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ የሚያከብሩት የጦርነት ህግ የለም!

በሌላ በኩል ግን ይሄ የሸማቂዎች መደበኛ የጦርነት ተፋላሚ አለመሆን የሚያስቀርባቸውም ነገር አለ፡፡ በዓለም ላይ ለጦርነት ተፋላሚዎች የሚሰጠው ህጋዊ ዕውቅናና መብት የላቸውም፡፡ በየሀገሩ ‹‹ህገወጥ›› ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ በራሳቸው ቆርጠው ነው የሚዋጉት፡፡ ከተያዙ ዓለማቀፍ የምርኮኛ መብቶች ላይኖራቸው ይችላል፡፡ በራሳቸው ቆርጠው ነው የሚዋጉት፡፡

ብዙ ጊዜ ግን - ይላል - እስከ እርሱ ዘመን የነበሩትን የዓለምን የሸማቂዎች መዳረሻ ያጠናው ክላውሶቪች - የሽምቅ ተዋጊዎች - በአብዛኛው የህዝብን የነጻነት ጥያቄ ይዘው ስለሚነሱ - የሚዋጉትን ጉልበተኛ መንግሥት አባርረው ሀገራቸውን በእጃቸው ያስገባሉ፡፡ አሊያም ጉልበተኛው መንግሥት ለድርድር እንዲቀመጥ ያስገድዱታል፡፡ አሊያም በአንድ ሀገር ውስጥ ካለ መንግሥት ጋር የሚዋጉ ከሆነም፣ ጉልበተኛውን መንግሥት ጥለው የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን የመረከብ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው! - ስለሆነም ‹‹ህገወጥ›› የሆነ ማንነታቸው ለዘለዓለም ተለጥፎባቸው የሚቀር ነገር አይደለም! በአሸናፊነታቸው ይፋቃል!

ክላውሶቪች የሚታወቀው የጦርነትን ምንነት፣ ስልቶችና መርሆዎች ቀምሮ በማስቀመጥ ነው፡፡ በቀጥታ የሽምቅ ውጊያዎችን በተመለከተ ‹‹የጎሪላ ተዋጊዎች ሁሉ ቅዱስ መጽሐፍ›› የሚባለውን የሽምቅ ውጊያ መርሆዎችና ስልቶች የጻፈው ሰው ደግሞ የቻይኖቹ ኮሙኒስት መሪ - ማኦ ነው፡፡ ማኦ ሴቱንግ (ዜዶንግ)!

ከቻይንኛ ወደ እንግሊዝኛ በተተረጎመውና ለዓለም የሽምቅ ተዋጊዎች ሁሉ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ በሚቆጠረው ‹‹The Baic Principles of Guerrilla Warfare›› በሚል ድርሳኑ፣ ማኦ የገበሬ ሠራዊቱን ይዞ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ፣ በአሜሪካኖችና በዓለም ኃያላን ሁሉ ከሚደገፈው ከሻንጋይሼኩ የኩሚንታንግ ናሽናሊስት መንግሥት ጋር ያደረገውን የደፈጣ ውጊያ ተጋድሎ ያወሳል፡፡ ሌሎች ህዝባዊ ትግልን አቀጣጥለው ወደ ደፈጣ ውጊያ የገቡ መጪ ትውልዶችና አብዮተኞች መከተል ያለባቸውን የደፈጣ ውጊያ ስልቶችና ስትራቴጂዎችም ይዘረዝራል ማኦ፡፡

‹‹የደፈጣ ውጊያ በተፈጥሮው ቀላል ነው፣ 
ቀላል መሣሪያዎችን ባነገቡ፣ እና ጥቂት 
ከባድ መሣሪያዎች በመሀላቸው ጣል ጣል 
በተደረገባቸው፣ ቁርጠኛ የህዝብ ልጆች 
አማካይነት የሚደረግ የማጥቃት ተግባር ነው፡፡

‹‹የደፈጣ ውጊያ ለሚካሄድበት አካባቢ መልክዓ
ምድርና፣ ነዋሪው ህዝብ እንደሚመች ተደርጎ
መካሄድ አለበት፡፡ እንደ ጊዜው አመቺነት፣ እና
ትክክለኛው ጊዜ እየተጠበቀም መከናወን አለበት፡፡
የደፈጣ ውጊያ 16 ባህርያት አሉት፣ እነዚህ ሁሉ
በአንድ ዐረፍተ-ነገር ሲጠቃለሉ ይህን ይመስላሉ፡-

‹‹ጠላት ወደኛ ይገሰግሳል፣ እኛ እንሸሻለን!
ጠላት ግስጋሴውን አቁሞ ካምፕ ሠርቶ ያርፋል!
እኛ እየመጣን ብሽሽቱን እየወጋነው እንሰወራለን!
ጠላት ይደክመዋል፣ እኛ ተጠናክረን እናጠቃለን!
በመጨረሻ ጠላት ያፈገፍጋል፣ እኛ እየተከታተልን 
እናሳድደዋለን፣ እምሽክ ሳናደርግም አንለቀውም!››

 — ማኦ ሴቱንግ፣ የደፈጣ ውጊያ መሠረታዊ መርሆዎች፣ ግንቦት 1928 
 
ማኦ ይሄን የደፈጣ ውጊያ መሠረታዊ መርህ የጻፈው፣ ለዘለዓለም የሚነቀንቀኝ የለም ያለውን የቻይናን መንግሥት፣ በደፈጣ ተዋጊ የገበሬ ሠራዊት ገርስሶ ሥልጣኑን ሊረከብ 20 ዓመት ሲቀረው ነው፡፡ የጃፓን ወራሪዎችን በደፈጣ ውጊያ ከቻይና ግዛት ጠራርጎ ከማስወጣቱ (በእርግጥ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ) ከ16 ዓመት ገደማ በፊት ማለት ነው፡፡

ማኦ - አንድ በደል የደረሰበት ህዝብ መሣሪያ አንስቶ የደፈጣ ውጊያ ከጀመረ - ከተማን ለቆ ወደ ገጠር መግባት አለበት - ይላል፡፡ ኮረብቶችን፣ ደለሎችን፣ ጉድባዎችን፣ ቁጥቋጦዎችን ይዞ ነው መዋጋት ያለበት የደፈጣ ተዋጊ፡፡ ከተማን ይዞ ከቆየ ግን - የመንግሥት መደበኛ ሠራዊት ፀሎቱ ሠመረለት ማለት ነው - ይላል ማኦ የራሱን ተሞክሮ እያስታወሰ፡፡

በ1927 ላይ (በእኛ በ1935 ዓ.ም.) የማኦ ደፈጣ ተዋጊዎች በትልቋ የሻንጋይ ከተማ የነበረውን የመንግሥት የጦር ሰፈር (ሚሊቴሪ ቤዝ) ከብዙ አቅጣጫዎች በማጥቃት ድምጥማጡን አውጥተው፣ ሻንጋይ ከተማን በቁጥጥራቸው ሥር አውለው፣ የኮሙኒስት ባንዲራቸውን ሰቅለው ነበር! ምን ዋጋ አለው? የመንግሥት ጦር አሉኝ የሚላቸውን ክፍለጦሮች ሁሉ ከያሉበት አሰልፎ በደፈጣ ተዋጊዎቹ ላይ ዘመተባቸው፡፡

በባሩድ አጭዶ፡፡ በታንክ ጨፈላልቆ፡፡ በእሳት ለብልቦ አልበቃውም የመንግሥቱ ሠራዊት፡፡ የደፈጣ ተዋጊዎቹን ደግፋችኋል ያላቸውን የከተማዋን ወጣቶችና የተማረ ኃይል ሁሉ ጨፈጨፈው! ማኦ በመጨረሻ ጨፍጫፊውን መንግሥት ድል አድርጎ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ እስካሁንም ድረስ ቻይናዎች ያከብሩታል ያንን ‹‹የሻንጋይ ከተማ ጭፍጨፋ››! እና ለማኦ እና ከዚያ በኋላ በዓለም ዙሪያ የማኦን መንገድ ለተከሉ የደፈጣ ተዋጊዎች ሁሉ የከተማ ደፈጣ ውጊያ የማይመከር ነገር ሆኖ ቀረ!