• 10 Oct, 2024

አባት ሀገር አማራ: -

አባት ሀገር አማራ: -

አማራ ማን ነው ?

inbound2051929552927205085
አባት ሀገር አማራ: -

1 በቂ የህዝብ ብዛት አለው :-

ያውም ታታሪ ሰራተኛ ፣ አርበኛ ፣ንቁ በትምህርት የሚያምን ፣ የመንግስትን መዋቅር የሚያውቅ በስርኣት የሚመራ፣ ሃገር ወዳድ…ከ54 ሚሊዬን የሚበልጥ ህዝብ አለው።

2 በቂ የተፈጥሮ ሃብት አለው: -

ከሁመራ ጀምሮ በወልቃይት በአርማጭሆ በቋራ አድርጎ እስከታች እስከ መተከል ድረስ የሚወርድ ሰፊ ድንግል የእርሻ መሬት አለን ። ጎንደር ፣ ጎጃም ፣ ሸዋ እና ወሎ… መሃል በተስማሚ የአየር ፀባይ ውስጥ የሚገኘው መሬታችን በዘመናዊ መንገድ ካመረትንበት እንኳን ለራሳችን ለብዙዎች እንተርፋለን። አሁን ባለው ኋላ ቀር አስተራረስ እዬተጠቀምን ለብዙዎች የምግብ ምርት አቅራቢ እኛ ነን። በከርሰ ምድር የውሃ ሃብት የናጠጥን ሃብታሞች ነን። በአፍሪካ ሶስተኛው በኢትዬጵያ አንደኛው ጨው የለሽ እርጎ የሆነ ሃይቅ… ጣና ከአማራ ልብ ነው ሚፈልቀው ። ፎገራ ፣ ደንቢያ፣ አለፋ ፣አቸፈር ፣ ባህርዳር አካባቢ ትንንሽ መስኖ ብንጠቀም ምርቱን ዝቀን አንጨርሰውም ። አባይ… አለማቀፉ ወንዝም የእኛ ንብረት ነው። ዋስ የሚሆን ወንዝ ነው አባይ! እሱን አሳይተን ብዙ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መሃበራዊ ትርፍ እናገኝበታለን ። ብዙ ያልተጠኑ ማዕድናትም መሬታችን ቀብራ ይዛለች ። የራሷ ልጆች በዘመናዊ መንገድ ቆፍረው እንደሚያወጧቸው አያጠራጥርም።

3 ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ ሀብት አለው: -

አማራ የማይጎበኝ ነገር የለውም ። ሰንሰለታማ ተራሮቹ (ከራስ ደጀን እስከ መንዝ ጓሳ ድረስ)ከነነፋሻ አየራቸው እና ከብርቅዬ የዱር እንሰሳቶቻቸው ጋር የቱሪስት ምግብ ናቸው። የጣና ገዳማት ፣ የጭስ አባይ ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተክርስትያናት ፣ የጎንደር ቤተ መንግስት ፣ የአላጥሽ በርሃ አናብስት… የቱሪስት መዳረሻዎቻችን ናቸው።

4 የነጠረ ቋንቋ ከነፊደሉ አለው: -

የራስ ቋንቋ ከነፊደሉ መያዝ ለእድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። የሃገሩን ህዝብም በቀላሉ እንዲግባባ በማድረግ ለጋራ እድገት ተደማምጠን እንድንቆም አማርኛችን ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከአለም አቀፍ የሳይንስ ቋንቋ ጋር እያዋሃድን የአማራን ህዝብ ከሳይንስ ጋር በቀላሉ እናሰልፈዋለን። ቋንቋ የትምህርት መሰረት ነው። ትምህርት ካለ ደግሞ ስልጣኔ ይኖራል። ቋንቋችን ለስነ ፁሁፍም የሰጠ ነው ። ስነ ፁሁፍ ደግሞ የህዝብ የመንፈስ ምግብ ፣ የማንነት ማሳያ ፣ የትስስሮሽ ገመድ… ነው። መፈላሰፊያ ቅኔ መቀኛ ስንኝ መቋጠሪያ ቋንቋ ከነ ፊደሉ ያለው አማራ በእውነት ሃብታም ነው። የአማርኛ ቋንቋችን የሃይማኖት ዜማዎች (መንዙማው፣ማህሌቱ) እና የሙዚቃ ዜማዎቻችን (ባቲ፣አንቺ ሆዬ ፣አምባሰል እና ትዝታ ) እንዳሻቸው የተንፈላሰሱበት ቋንቋችን ነው። ታሪካችን መዝግቦ ያስቀመጠልን ባለወግ ፣ባለ ስነ ቃል ፣ባለ ምሳሌ ፣እድሜ ጠገብ ቋንቋ ከነፊደሉ አለነን።

5 የሚያኮራ ታሪክ አለው: -

አባት ሀገር አማራ ከጥንት ስልጣኔ የሚመዘዝ ስር ያለው ምድር ነው። ታሪክ የሌለው ህዝብ ስነ ልቦናው ልል ሲሆን እንደ ሀገር ለመቆም ያስቸግረዋል። አማራ በዚህ አይታማም የታሪክ እጁ ረጅም ነው። የፈጠራ ታሪክ ሳይሆን የሚነበብ ፣ የሚዳሰስ ፣ የሚታይ ታሪክ ባለቤት ነው። የጥቁር ህዝብ የነፃነት ፋና ወጊ ፣ አይበገሬ ቆራጥ ፣ ጨዋ የነገስታት ህዝብ… አማራ ደረቱን ነፍቶ የሚያስኬደው የአኩሪ ታሪክ ባለቤት ነው። ታሪኩ የከፍታ እንጅ የዝቅተኝነት አይደለም ። ያለ ታሪክ የሚገነባ ሀገር በሚቀጥለው ቀን የረፈርሳል። አማራ ግን አለት የሆነ የታሪክ መሰረት አለው። ገና ያልተጠና ረብጣ ታሪክ ሞልቶታል።

6 ለዘመናት በፍቅር የኖሩ ዋና ዋና ሃይማኖቶች አሉት: -

አማራ ሁለት ዋና ዋና ድንቅ ሃይማኖቶች አሉት ። እስልምና እና ክርስትና በምድሩ ላይ ከአማራነት ጋር ሰምረው የሚኖሩ ናቸው ። ህዝቡ ለሃይማኖቶቹ ቅን ልቦና አለው። አማራ በሁሉም ሃይማኖቶቹ ለአለም ምሳሌ የሚሆኑ የበቁ የሃይማኖት አባቶች አሉት። ስነስርአት ያለው ህዝብ ነው። ከነዚህ ሁለት ዋና ዋና ሃይማኖቶቹ በተጨማሪ የአይሁድ እምነትንም ያራምዳል። ዛሬ በምድረ እስራኤል እና በአማራ ሀገር ያሉ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች ይሁዲነትንም ከአማራ ባህላቸው ጋር አጣምረው ለአለም ህዝብ ድንቅነታቸውን አሳይተዋል። የሃይማኖት መከባበር ያለበት ሃገር ሰላማዊ ነው። ሰላምዊ ሀገር ደግሞ ይበለፅጋል።

7 ውብ ባህል ፣ ቱውፊት እና እሴት አለው: -

የአማራ ባህል ከሰብአዊ መብት እና ከህግ ጋር የተስማሙ ናቸው።አማራ እድገትን የማይገዳደሩ ፣ ማህበረሰብን በፍቅር የሚያስተሳስሩ ፣ የአንድነቱ ማጣበቂያዎች… ባህል ትውፊት እና እሴት ሃብታም ነው።

አባት ሀገር አማራ እውን ይሆናል ስንል እነዚህን ሃብቶቻችን እያሰብን ነው። "የእገሌን ሃገር አታዩም ተገንጥሎ ምን አገኜ? " ለምትሉን መልሳችን #አባት_ሀገር_አማራ ለየት ይላል የሚል ነው።

#አባት_ሀገር_አማራ_ወይም_ሞት!!