• 10 Oct, 2024

አማራ እና ትግራይ Amhara & Tigray

አማራ እና ትግራይ Amhara & Tigray

አማራ እና ትግራይ ***************** © በሐይማኖትም፥ በባህልም፥ በአለባበስም የሚመሳሰሉ ብሔሮች ናቸው ትግራይና አምሓራ። ነገ ለሚያልፍ ፖለቲካ የብዙ ሺ ዘመን ታሪክ፥ ጊዜ የማይሽረው ግኑኝነትና ወዳጅነታችን ማጥፋት የለብንም። ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለ ፖለቲካ ሃላፊ ነው፥መንግስትም ያው ነው፥ ትምክህተኞችና ጠባቦችም ለጊዜው ናቸው፥ሃይማኖት ግን ለዘላለም ነው፥ህዝባውነትና መዋደድ ደግሞ እንዲሁ ዘላለማዊ ናቸው። ዕውር የሚመራው ዕውር እንዲሉ አንዳንድ አዋቂዎች ነን በሚሉ አንዳንድ አእምሮ የጎደላቸው፥ኃላፊነታቸውውም በትክክል በማይወጡ ጎጠኞችና ዘረኞች እንዲህ በየዋሁ ህዝብ ላይ የጠላትነት መንፈስ ላይ ዘርተው

አማራ እና ትግራይ 
*****************
© በሐይማኖትም፥ በባህልም፥ በአለባበስም የሚመሳሰሉ ብሔሮች ናቸው ትግራይና አምሓራ። ነገ ለሚያልፍ ፖለቲካ የብዙ  ሺ ዘመን ታሪክ፥ ጊዜ የማይሽረው ግኑኝነትና ወዳጅነታችን ማጥፋት የለብንም። ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለ ፖለቲካ ሃላፊ ነው፥መንግስትም ያው ነው፥ ትምክህተኞችና ጠባቦችም ለጊዜው ናቸው፥ሃይማኖት ግን ለዘላለም ነው፥ህዝባውነትና መዋደድ ደግሞ እንዲሁ ዘላለማዊ ናቸው። ዕውር የሚመራው ዕውር እንዲሉ አንዳንድ አዋቂዎች ነን በሚሉ አንዳንድ አእምሮ የጎደላቸው፥ኃላፊነታቸውውም በትክክል በማይወጡ ጎጠኞችና ዘረኞች እንዲህ በየዋሁ ህዝብ ላይ የጠላትነት መንፈስ ላይ ዘርተው አሁን በክፉ ዓይን መተያየት ጀምሯል። እንኳንም እንኳንስ በእምነት ከሚመስለው ይቅርና ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ተዋድዶና ተከባብሮ ይኖር የነበረውን የእምዬ ኢትዮጵያ ህዝብ ምድራዊና ሃላፊ በሆነውን  መሰረተ ቢስ ልዩነቶችን እያስተናገደ ይገኛል።እውነቱ ግን ሌላ ነው።የጋራ የሆኑ ድንቅና ውብ የሆኑ ሃይማኖታዊ መገለጫዎቻችን በተለይ በአምሓራ ክልል የሚገኙ የግሸንደብረ ከርቤ የጌታ ግማደ መስቀል መገኛ፥ታሪካዊው የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አበያተ ክርስቲያናት መገኛ፥የደጓ እናት ጻድቃኔ ማርያም ገዳም፥ሰው በቦታው ተቀብሮ የማይበሰብሰውና አፈር የማይበላው የጻድቁ አባታችን አቡነ መልከጼዲቅ ገዳም፥እንዲሁም ከላይ ክፍት ሆኖ ነገር ግን ውሃ የማይገባበት የአቡነ አሮን ገዳም፥ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ ብመባል የሚታወቁ የአባታችን አቡነ ተክለ ህይማኖት ገዳም፥የበረሃው ኮከብ ምድራዊ መልአክ የአባታዥን ወቡነ ገብረመንፈስቅዱስ ገዳም መገኛ...ኧረ ስንቱ... በትግራይ ምእመናን ላይ ከዓመት ዓመት ተወዳጅና በጉጉት የሚጠብቃቸው የአምላክ ስጦታዎች ናቸው። እንዲሁም በትግራይ ክልልም በሌላው ዓለም የሌለችው በአክሱም ብቻ ያለችው ታቦተ ጽዮን፥በመስተንክራዊ መልክዐ ምድር ያጌጠውና የአባታችን የአቡነ አረጋዊ  በሀገራችን የመጀመርያው የምንኩስና ገዳም፥የአብርሃ ወአጽብሃ ውብና አስደናቂ ገዳም፥የየሓ ቤተ መቅደስ፥በዕድሜ በ4ኛው መ.ክ.ዘ አባታችን አቡነ ገሪማ በእጃቸው እንደጻፉት የሚነገርለት የ4ቱ ወንጌላውያን የብራና መጽሐፍ፥የተሰዓቱ ቅዱሳን መናሃርያ፥የመስቀለ ክርስቶስ ገዳም፥ይማርያም ጉንዳጕንዶ ገዳም፥የሚካኤል እምባ ገዳም፥የኢትዮጵያ የመጀመርያ ጳጳስ የአባታችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ገዳም፥......በጣም ብዙ አሁን አርዝሬ የማልጨርሻቸው ቅዱሳት መካናት የሚገኙበት ከመሆኑም ሳቢያ በአምሓራ ውድ ህዝቦች ከዓመት ዓመት ይናፈቃሉ። 
@ እህህህህ....እውነትም ያማል....አሁንማ ወንድም በወንድሙ ላይ ጨከነ፥ህዝብ በህዝብ ላይ ተነሳ፥መንገድ ተዘጋ፥ከየትኛውን የአምሓራ ክልል ጤፍ/እህል በማንኛውም መልኩ ወደ ትግራይ እንዳይገባና እንዳይጫን ተከለከለ፥ከመቀለ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደውን መንገድ በወልዲያ አከባቢ ተዘግቶ የ 12:00 ሰዓት የነበረውን መንገድ ምስኪኑ የትግራይ ህዝብ በዓፋር ክልል የ17:00 ሰዓት ዙርያ ጥምጥም ጉዞ እየተጓዘ ነው።ለዚህች ለምታልፈው ዓለም በመሬትና በድንበር� "በየኔ ነው,,, የኔ ነው" የልጅ አስተሳሰብ ሳቢያ  ሊጥፋፋ በዓይን ቁራኛ እየተያየ ነው። ዜጎችም እንደፈለጉት ለመንቀሳቀስ እየተቸገሩ ነው፥ 12 ኛ ክፍል ላይ ወደ ከፍተኛ ተቋም ማለት ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎችም አሁን ስጋት ላይ ናቸው። ይህ ግን በስልጣን ላይ በተቀመጡ አንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው መሪዎች በወንድም ህዝብ እንደዚህ ካለ ደርጃ ደርሷል።
© እና ታዲያ ምብ ይሁን፦
...የሃይማኖት ሰዎች ነን የምንል፥እግዚአብሔርን እንፈራለን ብለን የምናስብ በዚህ ጉዳይ ላይ ከምንል ጊዜ በላይ ትኩረት በመስጠት ወደ ነበረው መተሳሰብና መቀራረብ እንዲመለስ ጥረት ማድረግ፥
© እንዲህ ህዝብ በህዝብ ላይ፥ወንድም በወንድም ላይ ዘረኝነትንና መለያየትን በሚዘሩ ምድራውያንና ሆድ አዳሪዎች ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ እንዚህ ሰዎችን በአጽንዖት መቃወምና ማስወገድ፥
©የሃይመኖት አባቶችና መሪዎች በቤተ እምነታዠው ልጆቻዠው ፍቅርንና መቻቻልን እንዲሰብኩ መንገርና ማነሳሳት
© መረጃና አሉባልታ ሁሉ አለማመን፥
© ከሁሉም በላይ ደግሞ የምናመልከው አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔርን በመፍራት እና ብመሳሰሉት መፍታት እንችላለን።
**********************************************
ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ
**********************************************
inbound5206657436118886216