• 10 Oct, 2024

ከዓለማችን ምርጥ መንደሮች የአንዱ መገኛ - ጮቄ‼

ከዓለማችን ምርጥ መንደሮች የአንዱ መገኛ - ጮቄ‼

🔘 ከዓለማችን ምርጥ መንደሮች የአንዱ መገኛ - ጮቄ‼

◉ ጮቄ ተፋሰስ እንደ ስነምህዳር ካየነው ከከሁለት እጁ እነሴ (ሞጣ) እስከ እንጅባራ የተዘረጋ ማማ ነው! በተለምዶ ጮቄ ተብሎ የሚጠራውን ክፍል ነጥለን ከተመለከትን ደግሞ ከ53,000 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ተፋሰስን አቅፎ በምስራቃዊው ጎጃም የተንጣለለ የሰማይ ጣሪያ ነው! ጮቄ የ273 ምንጮች እና የ59 ወንዞች መነሻ - የውኃ ማማ (water tower) ነው!

◉ ጮቄ 10 ያክል ወረዳዎችን የሚያካትት ሰፊ ተፋሰስ ነው! በዞን ከከፈልናቸው 9ኙ ወረዳዎች ከምስራቅ ጎጃም ሲሆኑ 1ዱ ደግሞ የምዕራብ ጎጃም አካል ነው! ወረዳዎቹም፦ ስናን፤ ቢቡኝ፤ እናርጅ እናውጋ፤ ሁለት እጁ እነሴ፤ ጎንቻ፤ ሰዴ፤ እነማይ፤ ማቻከል፤ ደባይ ጥላትግን - ከምስራቅ ጎጃም እንዲሁም ደጋ ዳሞት ወረዳ - ከምዕራብ ጎጃም ናቸው!!

◉ ከዚህ ውስጥ የማህበረሰብ ጥብቅ ደን (ስፍራ) ተብሎ በክልሉ እውቅና ተሰጥቶት የተካለለው የስነምህዳር ክፍል 6024 ሄክታሩ ብቻ ሲሆን በዚህ ወሰን ውስጥ የሚገኙ ወረዳዎች ደግሞ ስናን፤ ቢቡኝ፤ ሰዴ፤ ጎንቻ፤ እናርጅ እናውጋና ደባይ ጥላትግን ናቸው! ይሄ በጥብቅ ስፍራነት የተካለለው ክፍል በአዲስ አበባ - ደብረማርቆስ - ሮብ ገበያ መስመር ከአዲስ አበባ በ337 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል!!

◉ በዓለም ከሚገኙ ምርጥ የቱሪዝም መንደሮች ምርጡ መንደር የሚገኘው ከጮቄ ተፋሰስ ወረዳዎች በአንዱ በደጋ ዳሞት የጮቄ ክፍል ነው!! ይሄ መንደር በዚህ አመት ሊጎበኙ ከሚገባቸው የዓለም ምርጥ መንደሮች ምርጡ ሆኖ መመረጡን የምናስታውሰው ነው! መንደሩ በጥብቅ ስፍራነት ከተከለለው የጮቄ ተፋሰስ ውጭ መሆኑን ሳስብ በዚህ አይነትማ “አራት መከራክር ላይማ ተአምር መስራት ይቻላል” የሚል ገፊ ሀሳብ ይፈታተነኛል! ደግሞም ልክ ነኝ!!😑

◉ ጮቄ - የአባይ ዘብ! ጮቄ የግዮን ራስ! ጮቄ የምስራቅ አፍሪካ የውኃ ጋን! ጮቄ የጎጃም ሚዛነ ነፋስ ዘብ‼